Page 203 - አብን
P. 203

አብን


             4.2 ብሔራዊ ደኅንነትና መከላከያ


             4.2.1 የሰላምና የደኅንነት ጉዳይ የፖሊሲ አቅጣጫ

             የአንድ አገር የሰላምና ደኅንነት ፖሊሲ ከውጪ ጉዳይ ፖሊስ
             ጋር  ተመጋግቦ  መቀረጽ  አለበት፡፡  የሰላምና  ደኅንነት  የፖሊሲ
             አቅጣጫ  የአገር  ውስጥ  ፖለቲካዊ፣  ኢኮኖሚ፣  ማኅበራዊ  እና
             ጸጥታ  ነክ  ሁኔታዎችን  ከቀጣናዊና  ከዓለም  አቀፋዊ  ነባራዊ
             ሁኔታዎች  ጋር  ያናበበ  እንዲሆን  ይጠበቃል፡፡  በመሆኑም

             የአብን  የውጭ  ጉዳይ  እና  የደኅንነት  ፖሊሲ  ሰነድ  ሁለቱን
             ቁልፍ  ጉዳዮች  ከማመጋገብ  እኩል  የአገሪቱ  የሰላም  እና
             የደኅንነት  ፖሊሲ  ቅኝት  ከውጭ  ወደ  ውስጥ  ከውስጥ  ወደ
             ውጭ እንዲሆን ተሞክሯል፡፡

             4.2.1.1  የውስጥ  ደኅንነት  እና  የአገር  ውስጥ  የሰላምና

             ደኅንነት ተቋማት

             የኢትዮጵያ የሰላም እና የደኅንነት ጉዳይ አተያይ ከውስጥ ወደ
             ውጭ መሆን እንደሚገባው ይታመናል፡፡ የአገር ውስጥ ሰላምና
             ደኅንነት  በተለያዩ  ተፈጥሯዊና  ሰው  ሰራሽ  የሆኑ  ምክንያቶች
             ሊረበሽ  ይችላል፡፡  ኢትዮጵያ  በታሪክ  እንደአስከፊ  ድርቅ፣
             አምባገነናዊ  የፖለቲካ  ሥርዓት  የወለደው  ግጭት፣  የአገር
             ውስጥ  መፈናቀልና  ሞት፣  የኃይማኖት  እና  ብሔር  ግጭቶች

             ወ.ዘ.ተ.  ብዙ  አይነት  ውስጣዊ  ችግሮች  ሰላሟን  ሲነሱዋት
             የኖረችና አሁንም ከዚህ ያልተላቀቀች አገር ናት፡፡



             201    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   198   199   200   201   202   203   204   205   206   207   208