Page 198 - አብን
P. 198
አብን
እንደአለመታደል ሆኖ ያለፉት ሦስት አስርት ዓመታት
አገሪቱን እያስተዳደረ የዘለቀው ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝቦች
ዴሞክራሲያዊ ግንባር -ኢህአዲግ›› ወይም በአዲሱ ስያሜው
‹‹ብልፅግና ፓርቲ›› ዜጎች ሰላምና ደኅንነታቸው ተጠብቆ
የሚኖሩባትን አገር እንዲሁም የፍትኅ፣የጸጥታና የመከላከያ
ተቋማት ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ በእኩልነትና
በሕግ ማእቀፍ ላይ ተመስርተው የአገርና የዜጎቿን ሰላምና
ደኅንነት የሚያስጠብቁበትን ሥርዓት መገንባት አልተቻለውም፡
፡ ይልቁንም ገዥው መንግስት የፖለቲካ ስልጣኑን
ለማስጠበቅ ሲል ብቻ እነዚህን ተቋማት እንደመሣሪያ
በመጠቀምና ሕዝባዊ ወገንተኝነታቸውን በማሳጣት በሕዝቡ
ዘንድ አመኔታን የሌላቸው የኢ-ሰብዓዊነትና አድሏዊነት
መገለጫ ተቋማት ሆነው እንዲሳሉ አድርጓቸዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት አገሪቱ ሠላምና መረጋጋት የራቃት፣ ዜጎች
በማንነታቸው በግፍ የሚገደሉባት፣ኃብትና ንብረታቸው
የሚወድምባት፣ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸው
የሚጣስባት ሆናለች፡፡ የሕዝብ ለሕዝብ ሰላማዊ ግንኙነት
ተሸርሽሮ ጥርጣሬና ግጭት ተስፋፍቷል፡፡ የፍትኅና የጸጥታ
ተቋማት የመንግስት የጭቆናና የአምባገነናዊ ተግባር
ማስፈፀሚያ ሆነው እጅግ አሰቃቂ ሰብዓዊ ግፍ ሲፈፀም
ታዝበናል፡፡
ይህ ሁኔታም በሕዝብ ትግል ከአስከፊው የትሕነግ/ሕወኃት
አገዛዝ ከተላቀቅን በኋላም እጅግ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡
ለእልፍዓመታት በአብሮነት የተሰናሰለ የጋራ ታሪክና እሴት
196 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !