Page 200 - አብን
P. 200

አብን


             ደኅንነት  ግንባታውን  ‹‹ሀ››  ብሎ  የሚጀምረው  ‹‹ብሔራዊ

             እርቀ-ሰላምና መግባባት›› ከመፍጠር ይሆናል፡፡
                  ብሔራዊ  እርቀ-ሰላም  ማውረድና  አገራዊ  መግባባትን
                    መፍጠር

             የብሔራዊ እርቀ-ሰላምና መግባባት ጥያቄ ከደርግ ዘመን ጀምሮ
             አልፎ  አልፎ  በፖለቲካ  ጥያቄነት  ቢነሳም፣  ለአገር  ኅልውና
             መቀጠልና  ለብሔራዊ  ሰላምና  መረጋጋት  እጅግ  አንገብጋቢና
             ወሳኝ  የፖለቲካ  ጥያቄ  የሆነው  በኢሕአዲግ  የአገዛዝ  ዘመን

             ነው፡፡  የሕወኃት/ኢሕአዲግ  ከፋፍለህ  ግዛ  ዘይቤ  የሕዝብን
             አንድነትና  አብሮነት  በመሸርሸር  ግጭቶች  ማባባሱና  የአገሪቱ
             ሰላምና  መረጋጋት  ከጊዜ  ወደ  ጊዜ  አጣብቂኝ  ውስጥ  መግባቱ
             የብሔራዊ  እርቀ-ሰላምና  መግባባት  ጥያቄ  በተለያዩ  የፖለቲካ
             ድርጅቶች፣  ታዋቂ  ግለሰቦችና  የአገር  ሽማግሌዎች  ጭምር
             በየመድረኩ እንዲነሳ አድርጎታል፡፡


             አብን  ብሔራዊ  እርቀ  ሰላምና  አገራዊ  መግባባት  መፍጠር
             ወቅታዊና  አንገብጋቢ  የፖለቲካ  ጥያቄ  መሆኑን  በቅጡ
             ይገነዘባል፡፡ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችም ጥያቄውን በጥልቀት
             መርምረው ለዘላቂ አገራዊ ሰላምና መረጋጋት ብሎም ተቋማዊ
             የሥርዓተ-መንግስት  ግንባታ  ተቀዳሚ  ትኩረት  እንዲሰጡ
             ለማስቻል የፖለቲካ ፕሮግራሙና የምርጫ ማኒፌስቶው አካል
             አድርጎታል፡፡


             በመሆኑም ሕዝባችን በምርጫው ድምፁን ሰጥቶን ንቅናቄአችን
             የመንግስት ስልጣን ሲይዝ ከተቋማት ግንባታም ሆነ ከአገራዊ


             198    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   195   196   197   198   199   200   201   202   203   204   205