Page 195 - አብን
P. 195
አብን
እንዲኖረው አስፈላጊ ሕጋዊና ተቋማዊ መስመሮች
ይዘረጋሉ።
ወጣቶች ሕብረተሰባዊ ግልጋሎት (community
service) መስጠት እንዲችሉ፣ በከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት ሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ እንዲካተት
ይደረጋል፤ ሌሎችም አስፈላጊ ሁኔታዎች ይመቻቻሉ።
ወጣቶች ልዩ ተሰጥኦዎቻቸውንና እምቅ ችሎታቸውን
የሚያዳብሩባቸውና የሚያሳዩባቸው መድረኮች
ይዘጋጃሉ።
የወጣቶችን የሥራ እድል ለማስፋትና ሥራ አጥነትን
ለመቅረፍ አስፈላጊው ጥረት ይደረጋል።
3.16 አካል ጉዳተኝነት
አካል ጉዳተኞች ለአገራቸው ሰፊ አበርክትኦት
እንዳላቸው አብን ያምናል፡፡ በመሆኑም አካል
ጉዳተኞች በሁሉም መስክ ተገቢውን ተሳሰተፎ ያደርጉ
ዘንድ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ይደረጋል፡፡
የአካል ጉዳተኛ ማኅበራት እንዲጠናከሩ የማበረታቻ
ማዕቀፎች ተግባራዊ ይሆናሉ ፡፡
የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ የሚያሳድግ ልዩ
የትምህርት ዘርፍ ማዕቀፍ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እና ሌሎች
የኮንስትራክሽን ሥራዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ
ያደረጉ እንዲሆኑ አስገዳጅ መመሪያዎች ይወጣሉ፡፡
ለአካል ጉዳተኝነት መንስኤ የሚሆኑ ችግሮችን
በመለየት ለመቀነስ እና ለማስቆም የሚያስችሉ
193 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !