Page 193 - አብን
P. 193
አብን
ብሔራዊና አካባቢያዊ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቻናሎች
በልዩ ልዩ አገራዊና የውጭ ቋንቋዎች ሥርጭት
እንዲኖራቸው ይደረጋል።
ለፕሬስ ለብቻው ሕግ ማውጣት ሳያስፈልግ በአገሪቱ
ሕጎች ይዳኛል።
ለፕሬስ እድገት አስፈላጊው የትምህርትና ምርምር
ፕሮግራሞች ይቀረጻሉ።
የተሰደዱ ጋዜጠኞች ወደ አገራቸው ተመልሰው
እንዲሰሩ ይበረታታሉ።
ዓለምአቀፋዊ ሚዲያዎች (እንደ ቪ ኦ ኤ፣ ቢቢሲ፣
ዶቸቨሌ፣ ወዘተ.) ስርጭት ይበረታታል።
3.13. ኃይማኖት
መንግስትና ኃይማኖት የተለያዩ ናቸው::
የኃይማኖት ተቋማት በሰላምና ልማት ስራዎች
አስተዋጾ እንዲያደርጉ ይበረታታሉ።
የኃይማኖት መሪዎችና ምእመናን ጽንፈኝነትን
እንዲከላከሉ ይበረታታሉ።
የሕዝብ ማምለኪያና የመቃብር ስፍራዎች ከክፍያ ነጻ
ይሆናሉ።
የኃይማኖት ተቋማት የአገሪቱን ብሔራዊ አንድነትና
ሰላም፣ በሕዝቡም መካከል ፍቅርና ሕብረት
እንዲጠናከር እንዲሰሩ ይበረታታሉ።
3.14. ሴቶች
191 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !