Page 188 - አብን
P. 188
አብን
ሰላማዊ አብሮነትን ማጠናከር በሚያስችል መልኩ
ለማደራጀት ጥረት ይደረጋል።
ለባሕላዊ ጨዋታዎችና ውድድር እውቅና በመስጠት
በያካባቢውና በብሄራዊ ደረጃ የውድድር መርኃ-ግብሮች
እንዲዘረጉ ይደረጋል።
ኢትዮጵያ በዓለም የስፖርት ውድድር ያላትን እውቅና
የበለጠ ለማሳደግና ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶ
ይሰራል።
ልዩ ልዩ ስፖርታዊ ፌደሬሽኖች ከማናቸውም የፖለቲካ
ጫና ነጻ እንዲሆኑ ይደረግጋል።
የግል ባለኃብቶች በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች መዋእለ
ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ይበረታታሉ።
ልዩ ልዩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችና መዝናኛ
ፓርኮች ይገነባሉ።
የስፓርት ትምህርት ከፍተኛ ተቋማት ይገነባሉ።
የስፖርት ሙዚየሞችን በየአካባቢው ለማቋቋምና
ለማስፋፋት ጥረት ይደረጋል።
3.9. ኪነ-ጥበብ
የኪነ-ጥበብ ሥራዎች፦ ቲያትር፣ ሙዚቃ፣ ሥነ-
ጽሁፍ፣ ፊልም፣ ሥነ-ስእል እንዲሁም ሌሎች የፈጠራ
ሥራዎች እንዲጠናከሩ አስፈላጊው ጥረትና እገዛ
ይደርጋል።
የአእምሮ የፈጠራ ውጤቶች ባለቤትነት በሕግ
ይጠበቃል።
ልዩ ልዩ የፈጠራ ሥራ ትምህርት ተቋማት ይገነባሉ።
186 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !