Page 185 - አብን
P. 185
አብን
የኢትዮጵያ ሕዝቦች በዘመናት ውስጥ ያለፉባቸው በርካታ
ሥልጡን ባሕሎች የጋራ ኃብቶቻችን መሆናቸውን
እንገነዘባለን፤ በአንድነት ልንጠብቃቸውና ልናዳብራቸው
የሚገቡ መሆናቸውንም እናምናለን። በኢትዮጵያዊ
ወንድማማችነት መንፈስ የአንዱ ባሕል የሌላው፣ የሌላኛው
ደግሞ የአንዱ ባሕል መሆን እንደሚገባው እናምናለን፡፡ ይህንን
በጎ ትልም የምናሳካው ሁሉም ባሕሎች የሁላችን መዋቢያ እና
የጋራችን አገራዊ ኃብቶች መሆናቸውን አውቀን በተገቢው
መልኩ እንዲያድጉ፣ እንዲጠበቁና ከትውልድ ትውልድ
እንዲተላለፉ ስናደርግ ነው፡፡ በባሕሎች መካከል የበላይና
የበታች እንደነበረ የተነዛውን የፈጠራ እና የጨቋኝ-ተጨቋኝ
ትርክት አሽቀንጥረን በመጣል በመደማመጥ፣ መከባበርና
መተማመን ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትን
በመገንባት የወደፊት የጋራ ተስፋችንን ብሩኅ እናደርጋለን፡፡
ኢትዮጵያውያን በታሪክ ሂደት ውስጥ ያካበቷቸው ቅርሶች፣
ኃይማታዊና ታሪካዊ ኃብቶች፣ ሚዳሰሱና የማይዳሰሱ
ኃብቶች፣ የተፈጥሮ ኃብቶች፣ የዱር እንስሳት፣
የኢትዮጵያዊነት መገለጫዎች ሁሉ በከፍተኛ ትኩረት
ተጠብቀው ለመጪው ትውልድ በክብር እንዲተላለፉ
እናደርጋለን፤ ለዚህም መላው ሕዝባችንን በባለቤትነት
ያሳተፈና ከዘርፉም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ
ልዩ ልዩ ዘርፈ ብዙ የፖሊሲ ድጋፎችንና አሰራሮችን
እንዘረጋለን፡፡ የመኖሪያ ሰፈር ግንባታዎች፣ የሥራ እድል
ፈጠራዎች፣ የኢንቨስትመንት ሥራዎች እንዲሁም
የሥልጣኔና ዘመናዊነት መስፋፋቶች በሚፈፀሙበት ጊዜ ነባር
183 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !