Page 183 - አብን
P. 183

አብን


             ተቀባይነት፣  ኩሩነትና  ጀግነት፣  መንፈሳዊና  ቁሳዊ  ባሕሎች

             እና  መሰል  ኃብቶች  በአገራችን  ሕዝቦች  የዘመናት  ታሪክና
             ባሕል  ውስጥ  ያሉ  ከመሆናቸው  በላይ  አብዛኞቹ  ተወራራሽና
             ለአገር  እድገት፣  ግንባታና  አንድነት  የበኩላቸውን  ያበረከቱና
             ወደፊትም የሚያበረክቱ ናቸው፡፡

             ባለፉት  29  ዓመታት  በአገራችን  ላይ  ሰፍኖ  የነበረው  ከፋፋይ
             ሥርዓት        በብሔረሰቦችና         ባሕላቸው        መካከል       ልዩነትን
             በመዝራት  ላይ  ያተኮረ  ስለነበር  የኢትዮጵያ  ብሔሮችና

             ብሔረሰቦች  ባሕላቸውን  በትክክል  የሚያሳድጉበት፣  ለአገር
             አንድነትና  ኅብራዊነት  በስፋት  የሚጠቀሙበት  አስቻይ
             ፖሊሲና አሰራር አልተተገበረም፡፡ በብዝኃነት ውስጥ የሚኖርን
             ዥጉርጉር  ውበት  ለአገር  አንድነት  ግንባታ  ከማዋል  ይልቅ
             ለጥርጣሬና  መለያያ  ብሎም  ለግጭት  ግብዓት  ያዋለው  ይኼ
             ሥርዓት  በተለይ  የአማራን  ሕዝብ  በጎ  ኢትዮጵያዊ  ባሕል

             በሌሎች ብሔረሰቦች ላይ የተጫነ እና ጨቋኝ አድርጎ የሐሰት
             ትርክትን አቀናብሮ በማቅረብ ለአገር ኅልውና ጭምር ስጋትን
             እንደፈጠረ  ይታወቃል፡፡  ከ2010  ዓ.ም  አጋማሽ  ገደማ  መጣ
             የተባለው  «ለውጥ»ም  ቢሆን  ከዚህ  የዘለለ  ነገር  ሲፈጽም
             አልታዬም፡፡  በመሆኑም  በአገራችን  ኢትዮጵያ  የአንዱ  ባሕል
             በሌላኛው ላይ የተጫነ ተደርጎ ሲነዛ የነበረው ጊዜ ያለፈበትና
             አገር አፍራሽ የሐሰት ትርክት ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ ምድር
             ዳግም ለእኩይ ዓላማ ማስፈጸሚያነት ተግባር ላይ እንዳይውል

             እንሰራለን፡፡





             181    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   178   179   180   181   182   183   184   185   186   187   188