Page 179 - አብን
P. 179
አብን
ሥራ ላጡ ዜጎች ሥራ አፈላላጊና መረጃ ሰጪ ቡድን
በየአካባቢው (በታችኛው የስልጣን ርከን ወይም ቀበሌ)
ይቋቋማል።
በስራ ላይ የአካል ጉዳት ለሚያጋጥማቸው ዜጎች
የማኅበራዊ ዋስትናና ካሳ መብት ይጠበቃል።
አገራቸውን በተለያየ መስክ ሲያገለግሉ የኖሩና በጡረታ
የተገለሉ ዜጎች፣ ክበብ አየፈጠሩ መንፈሳቸውንና
ኣካላቸውን እንዲያዝናኑ ይደረጋል፤ ክፍያቸውም
የወቅቱን ኑሮ ደረጃ ያገናዘበ እንዲሆን ይደረጋል።
የሕፃናት ጎዳና አዳሪነት በሕግ ይከለከላል፤ ለወላጅ/አሳዳጊ
አልባ ሕፃናት በየአካባቢያቸው ጥበቃና ክብካቤ ይደረጋል።
ሕገ-ወጥ የሰዎች ልውውጥ/ዝውውር (human
trafficking) እንዲጠፋ ለማድረግ የተቀናጀ ጥረት
ይደረጋል።
የጤና ኢንሹራንስ ካምፓኒዎች ይመሰረታሉ፤ ለሕክምና
መክፈል የማይችሉ ዜጎች ሕክምና በነጻ እንዲያገኙ
ይደረጋል።
3.5. የምግብ ዋስትናና አደጋ መከላከል ፖሊሲ
በፖለቲካ አለመረጋጋቶች፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖ፣
የበረኃ አንበጣ መንጋ ያስከተለው ውድመት እንዲሁም
177 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !