Page 175 - አብን
P. 175
አብን
ብቁና ተወዳዳሪ መምህራንን ለማፍራት አስቻይ አሰራሮች
በሥራ ላይ ይውላሉ፡፡
ልዩ ማበረታቻዎችንና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን
በመስራት የሚስተዋለውን የሴቶች ተሳትፎ
ከዴሞግራፊያዊ ምጥጥኑ ጋር የሚያስተካከል እንዲሆን
ይደረጋል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሁም ሥራ
ፈጣሪ ምሩቃንን ሊያፈራ በሚያስችል አደረጃጀት
ይዋቀራል፡፡ የዜግነት አገልግሎትና ሥራ ልምምድ
የከፍተኛ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀረፃል፡፡
መምህርነት የተከበረ ሙያ ሆኖ እንዲቀጥልና ሙያውን
ብቃት ያላቸው ዜጎች መርጠውት እንዲቀላቀሉ
የሚያስችሉ ሁሉን አቀፍ ሥራዎች ይሰራሉ፡፡
ትምህርት የኅብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ባለቤትነት
በሚያረጋግጥ አመራርና አደረጃጀት እንዲመራ ይደረጋል፡፡
የትምህርትን ፍትኃዊ ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ
አስቻይ ከአገሪቱ ጥቅል ዓመታዊ ገቢ ጋር አብሮ እያደገ
የሚሄድ በጀት የሚመደብ ይሆናል፡፡
መማር ማስተማር ውጤታማ የሚሆነው የትምህርት
ማስኬጃ ግብዓት በበቂ ሁኔታ ሲሟላ ነው፡፡ የትምህርት
173 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !