Page 176 - አብን
P. 176
አብን
ጥራት እና ፍትኃዊ ተደራሽነት እንዲጠበቅ መሟላት
ስላለባቸው ግበዓቶች በመለየት ተግባራዊ እንዲሆኑ
ይደረጋል፡፡
የትምህርት አመራሩ አሁን ያለውን ውስብስብና
ተለዋዋጭ የዓለም ሁኔታ በመረዳት ተወዳዳሪና ውጤታማ
ሆኖ ለመውጣት አስቻይ ብቁ አመራር እንዲሆን ባለድርሻ
አካላትን ያሳተፉ ሥራዎች ይሰራሉ፡፡
3.3. ሲቪል ሰርቪስ
የሰው ኃይል ገበያን ማጠናከርና የፈጠራ ሥራን
ማበረታታት።
በሁሉም ሴክተሮች የሙያ ብቃትና ውጤማነት
ማሻሻያ ትምህርትን ማጠናከር፤ ማሳደግ።
በሁሉም ሴክተሮች የሥራና የፈጠራ ከባቢዎችን
በመፍጠር ምርትን ማሳደግ።
የማህበራዊ-ድር ሥራዎችን በማጠናከር ሰርቪስ
ሴክተሩ ምርታማ እንዲሆን ማድረግ።
ጥራትን፣ የሥራ ቅልጥፍናን፣ ፍትኃዊነትንና
ተገቢነትን መሰረት ያደረገ ሥራ እንዲሰራ ማድረግ።
ሥራና ሰራተኛ እንዲገናኙ ማድረግ።
ግልጽና ፍትኃዊ የዕድገት መሰላሎችን ለሰራተኞች
መዘርጋት።
174 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !