Page 174 - አብን
P. 174
አብን
ተከታታይ ዓመታት ከ1ኛ እሰከ 6ኛ ክፍል ይከታተላሉ፡፡
ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል የሚሰጠው ትምህርት መሰረታዊ
ችሎታ ያላቸውን ዜጎች የሚያፈራ ሆኖ ይዘጋጃል፡፡ የ6ኛ
ክፍል ተማሪዎች የቅድመ-መጀመሪያ የሆነውን ትምህርት
ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ተዘጋጅቶላቸው እንዲፈተኑ
ይደረጋል፡፡
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በሁለት ደረጃ ተከፍሎ የሚሰጥ
ሲሆን 7ኛ እና 8ኛ ትምህርቶች የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት (Junior secondary education)፣ የ8ኛ ክፍል
ተማሪዎቸ አገር አቀፍ ፈተና ተዘጋጅቶ በከፍተኛ ሁለተኛ
ደረጃ (ከ9ኛ እስከ 12ኛ) የሚሰጠው ትምህርት ተማሪዎችን
በኮሌጅ፣ በዩኒቨርሲቲ እና ለሥራ ማዘጋጃ ሙያ ስልጠና
(Vocational preparation for the job) ከፍተኛ
ትምህርት በብቃት የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ፖሊሲ የሚስተዋሉትን
የተማሪ የጥራት፤የፍትሃዊነት፤ተገቢነትና ተደራሽነት
ችግሮችን ለመቅረፍ ይሰራል፡፡
የተማሪዎችን ንቁ ተሳትፎ የሚያረጋግጡ የትምህርት
አቀራረቦች ይተገበራሉ፡፡
172 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !