Page 178 - አብን
P. 178
አብን
የሚሰበሰበው ገንዘብ በየጊዜው የሚጨምርበትና ዘላቂነቱ
የሚያረጋግጥበት ሕጋዊ አደረጃጀትና አሠራር ይፈጠራል።
የጡረተኞች አበል በየጊዜው ከሚፈጠረው የኑሮ ውድነት
ጋር በሚጣጣም መንገድ ማሻሻያ ይደረግበታ።
አሁን በሥራ ላይ ያለው የማኅበራዊ ዋስትና ፖሊሲ፣
የፖሊሲው ማስፈፀሚያ ሕጎችና መዋቅሮች እንዲሻሻሉና
በጠንካራ መሠረት ላይ የቆመ የማኅበራዊ ዋስትና ፖሊሲ፣
አደረጃጃትና አሠራር እንዲኖር ይደረጋል።
ኢትዮጵያውያን ሁሉ የማኅበራዊ ዋስትና ቁጥር
ይሰጣቸዋል፤ ግለሰባዊ መረጃቸውም በዘመናዊ መረጃ
ኣያያዝ በኮምፒውተር ይሰነዳል።
ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል መኖርም
ሆነ መሥራት፣ እንዲሁም የመኖሪያና መስሪያ
አካባቢያቸውን እንደየፍላጎታቸው መቀያየር፣ መዘዋወርና
መወሰን ይችላሉ።
በሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አደጋ የተፈናቀሉ ወገኖችን
መልሶ ለማቋቋም አስፈላጊው እገዛ ይደረጋል።
የማኅበራዊ ደኅንነት ዋስትና ጽህፈት ቤቶችን በመክፈት፣
አቅም በፈቀደ መጠን ለአረጋውያን፣ ወላጅ ያጡ ህጻናትና
የጎዳና ተዳዳሪዎች አስፈላጊው እርዳታና ክብካቤ
ይደረጋል።
176 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !