Page 171 - አብን
P. 171
አብን
ትምህርትና ሥልጠና ከማኅበረሰብና ከአገር ልማት ጋር
ተገቢው ትስስር እንዲኖራቸው በማድረግ የማኅበራዊ፣
ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገትን ማፋጠን፤
ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት የማመዛዘን፣
የመፍጠርና የመመራመር ችሎታን በማዳበር
የኢትዮጵያን የሰለጠነ የሰው ኃይል ማሳደግ፤
የትምህርት ፖሊሲ
በአገራችን በትምህርት በኩል የታዩ ዘርፈ-ብዙ ችግሮችን
ለመፍታት እና ለመለወጥ ተስማሚ የትምህርት ሥልጠና እና
ፖሊሲ አስፈላጊ በመሆኑ፤ የትምህርት ፖሊሲው ከመዋለ-
ሕፃናት ጀምሮ እሰከ ከፍተኛ የዩኒቨርስቲ ትምህርት ያለውን
ጨምሮ መደበኛ እና መደበኛ ያልሆኑ ትምህርት አጠቃላይ
እና ዝርዝር ተግባሮችን እና ዓላማዎችን እንዲሁም ስልቶችን
ጠቅልሎ በሚያሳይ መልኩ መዘጋጀት አለበት ብሎ አብን
ያምናለ፡፡
ማንኛውም ሰው ትምህርት የማግኘት ዕድል እንዲኖረው
ይደረጋል፡፡ ማንኛውም ወላጅ ወይም አሳዳጊ የሚያሳድጋቸውን
ልጆች ትምህርት እንዲያገኙ የማድረግ ግዴታ ይጣልበታል፡፡
ሥርዓተ-ትምህርቱ ሲዘጋጅም፣ ሲተገበርም፣ ሲገመገምም
ኅብረተሰቡን በሰፊው በማሳተፍ ተወዳዳሪነትን የሚያመጣና
ጥራቱን የጠበቀ የትምህርት ሥርዓት እንዲኖር ይደረጋል፡፡
ዓለምአቀፍ ደረጃዎችን አገናዝቦ፣ አገርአቀፍና አካባቢያዊ
ጭብጦችንና ፍላጎትን አካቶ ሥርዓተ-ትምህርቱ በየደረጃው
169 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !