Page 172 - አብን
P. 172

አብን


             በትምህርት        እርከኖች       መካከል       መወራረስና         መደጋገፍ

             እንዲሁም  ተመጣጣኝነት  /ስታንዳርድ/  እንዲጠብቅ  ሆኖ
             ይዘጋጃል፡፡

             የትምህርት  ሥርዓቱን  እና  ጥራቱን  በጠበቀ  መልኩ
             መመዘኛውን  ለሚያሟሉ  የግል  ባለሀብቶች  የትምህርት
             ኢንቨስትመንት  ላይ  እንዲሰማሩ  ይደረጋል፡፡  ሥርዓተ-
             ትምህርቱ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ተላቆ በሙያው ባለቤቶች
             ብቻ እንዲመራ ይደረጋል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት በአፍ

             መፍቻ  ቋንቋ  እንዲሰጥ  ይደረጋል፡፡  ለሒሳብ፣  ሳይንስና
             ቴክኖሎጅ  ትምህርቶች  ልዩ  ትኩረት  ይደረጋል፡፡  ለአካል
             ጉዳተኞች፣ ሴቶችና የላቀ ተሰጥዖ ያላቸውንና ከፍተኛ ውጤት
             የሚያስመዘግቡ  ተማሪዎችን  የሚያበረታታ  የልዩ  ድጋፍ
             አሰራር ይዘረጋል፡፡


             መኃይምነትን  ለማጥፋት  ከመደበኛው  የትምህርት  ሥርዓት
             ጎን  ለጎን  የጎልማሶች  ትምህርት  ልዩ  ትኩረት  ተሰጥቶት
             እንዲሰራበት  ይደረጋል፡፡  ከዚህ  በተጨማሪ  የሕዝቡ  ቀደምት
             የእውቀትና ጥበብ ምንጭ የሆኑት የአብነት ትምህርት ቤቶችና
             መድረሳዎች  በልዩ  ትኩረት  ድጋፍ  ይደረግላቸዋል፡፡  የቆየ
             ማንነታቸውን  ለቀጣይ ትውልድ ያስተላልፉ ዘንድ አቅማቸው
             እየተገመገመ ወደ ከፍተኛ የትምህርትና የምርምር ማዕከልነት
             ደረጃ  ሊያድጉ  የሚችሉበት  አሰራር  ይዘረጋል፡፡  እድሜ  ጠገብ

             አዛውንቶች  በእድሜያቸው  የቀሰሙትን  እውቀት  ለትውልዱ
             የሚያስተላልፉበት መንገድ በተለየ መልኩ ትኩረት ተሰጥቶት
             ይሰራበታል፡፡


             170    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   167   168   169   170   171   172   173   174   175   176   177