Page 184 - አብን
P. 184
አብን
ኢትዮጵያን በክብር ያኖረና የሚያኖር የኢትዮጵያውያን
የጀግንነት ታሪክ እንደተረት ተረትና አልባሌ ነገር ተደርጎ
ሲቀርብ የነበረው እኩይ ምስል እንዲስተካከል ይደረጋል፤
የኢትዮጵያውያን የአገርን ሉዓላዊነት ያስጠበቀና የሚያስጠብቅ
የተጋድሎ ባሕል በክብር ይዘከራል፡፡ የኢትዮጵያውያን
የአንድትና የመተባበር እንዲሁም የአገር ፍቅርና የድል
አድራጊነት ባሕል የተዘከረባቸው አውደ ውጊያዎች ማለትም
የጥቁር ሕዝቦች የነፃነትና የአሸናፊነት ምልክት የሆነው
የአድዋ ድል በዓል፣ የካራማራ፣ የአምስቱ ዓመት የኢትዮ-
ጣሊያን ጦርነት ድል እና መሰል ሕዝባዊ/አገራዊ ድሎች
ለትውልድ ይዘከራሉ፡፡ የአገር ባለውለታ ጀግኖችም በክብር
ከትውልድ ትውልድ ይታወሳሉ፡፡ በሉላዊነት ሳቢያ የራሱን
እንቁ ባሕል ንቆ /ትቶ/ ጎጂ መጤ ባሕልን የሚያንጠለጥል
ትውልድ እንዳይፈጠር፤ ይልቁንም ወጣቱ አገራዊ በሆኑ
ቁሳዊና መንፈሳዊ የማንነቱ አስኳል በሆኑ እሴቶቹና አሻራዎቹ
ላይ እንዲያተኩር ይሰራል፡፡
ኢትዮጵያዊ ውበታችን በሆኑ አኩሪ ባሕሎቻችን፣ የብሔር
ስብጥር ልዩነታችን፣ ቋንቋዎቻችን እንዲሁም ኃይማኖቶቻችን
ብዝኃነቶች ሰበብ በማድረግ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን
ለመከፋፈል የሚደረገውን ሕግና መዋቅር ወለድ መንግስት-
አገዝ ሽብርና ማኅበራዊ ሁከት በማውገዝ የኢትዮጵያዊነት
ብሔራዊ ስሜታችንን የሚያበለጽግ ኅብረብሔራዊ ፀጋዎቻችንን
እናጎለብታለን፤ የኢትዮጵያን ባለብዙ ቀለም አንድ
አገርነትንም እናጸናለን፡፡
182 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !