Page 186 - አብን
P. 186
አብን
ታሪካዊ፣ መንፈሳዊና ተፈጥሯዊ፤ ቁሳዊና መንፈሳዊ
(የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ) ቅርሶችና ባሕሎችን በማይጋፉና
በማይፃረሩ መልኩ ይፈፀማሉ፡፡ የጋራ ኢትዮጵያዊነት እሴትን
ለመግንባት የሚረዱ ባሕሎች፣ ወጎች፣ ልማዶች፣
ትውፊቶች፣ እሴቶችና አሰራሮች በሥርዓተ-ትምህርት ተካተው
ለትውልድ ግንባታ እንዲውሉ ይደረጋል፡፡
3.7.2. ቋንቋ
ኢትዮጵያ የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ የብዙ ብሔረሰቦች
አገር ናት። ለሺህ ዘመናት የቆዬ የራሷ አገር በቀል ፊደላት
እና ሥርዓተ-ጽሕፈት ያላት በመላው ዓለም ላሉ ጥቁር
ሕዝቦች የኩራት ምንጭ የሆነች አገር ናት፡፡ የራሷን ሆሄና
ሥርዓተ-ጽሕፈት ተጠቅማ የፃፈቻቸው ሺህ ዘመናትን
ያስቆጠሩ ጥንታዊ ጽሑፎችም ያላት ናት፡፡ ቋንቋ
ከመግባቢያነት ባሻገር ከባሕልና ማኅበረሰባዊ ማንነት ጋር
የተቆራኘ እንደመሆኑ እንዲጠበቅ፣ እንዲስፋፋና እንዲበለጽግ
የቋንቋ አጠቃቀምና ማበልጸጊያ ፖሊሲ እንተገብራለን፡፡
የኢትዮጵያ ኃብቶች የሆኑ ሁሉም ቋንቋዎች በሕግ ፊት እኩል
ሆነው እንዲያድጎ እንሰራለን፡፡ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች
ለትምህርት አገልግሎት እንዲውሉ ይደረጋል፡፡
በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል የሚነገረውና በኢትዮጵያ ዋና
ዋና ከተሞች ደግሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሆነው አማርኛ
ብሔራዊ ቋንቋ ይሆናል፡፡ ጥናትን መሰረት በማድረግ
በብሔራዊ ደረጃ ተጨማሪ የሥራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ
ይደረጋል፡፡ የማኅበረሰባዊ ስብጥርን ታሳቢ ባደረገ መልኩ
184 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !