Page 205 - አብን
P. 205
አብን
4.2.1.2 የአገር መከላከያ፣ የመረጃና ደኅንነት ተቋም የፖሊሲ
አቅጣጫ
ሀ) የምድር ኃይል እና የአየር ኃይል
ከ1983 ዓ.ም. ወዲህ ዋነኞቹ የኢትዮጵያ የመከላከያ ተቋማት
የምድር ኃይልና የአየር ኃይል እንደሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
አብን በመጭው ዘመንም እነዚህ የመከላከያ ክፍሎች የአገሪቱን
ደኅንነት በማስጠበቁ ሂደት ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚወስዱ
ይገነዘባል፡፡ በዚህ መነሻነት አብን ሁለቱም ተቋማት የዓለምን
የነባራዊ ሁኔታዎችና ዘመኑ የደረሰበትን የቁሳቁስ፣
የቴክኖሎጂና የእውቀት ትጥቆች ባገናዘበ መልኩ እንዲደራጁ
ይሰራል፡፡ በየጊዜው ከአገሪቱ ተጨባጭ የደኅንነት ስጋት፣
ከጸጥታ አጠባበቅና ከፖለቲካ አንድምታቸው አንፃር በሚሰሩ
ጥናቶችና ትንተናዎች ላይ በመመስረት አቋማቸውን ያሻሽላል፡
፡
ለ) ባሕር-ኃይል
አብን የኢትዮጵያ ባሕርኃይል ኅልውና በኢትዮጵያ ፍላጎት ላይ
ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ የክልላዊ ዲፕሎማሲ ተጽእኖ
ፈጣሪነትን በማሳደግ የባሕርኃይሉ ይበልጥ የተደራጀና ቢያንስ
በቀጠናው ተገዳዳሪ ቁመና ያለው ተቋም እንዲሆን ማድረግ
እንደሚገባ ያምናል፡፡
203 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !