Page 206 - አብን
P. 206
አብን
ሐ) ወታደራዊ የውጭ ስልጠናዎች
አብን ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በሰራዊቱ ላይ ይታይ
የነበረውን የገለልተኝነት ችግር መቅረፍ የሚያስችሉ
የኢንዶክትሪኔሽን ሰነዶችን አዘጋጅቶ ከማሰልጠን የሚጀምር
ተከታታይነት ያለው በአስተሳሰብ ላይ የሚደረግ
ኢንቨስትመንት አንዱና ዋናው ቁልፍ ሥራ መሆን እንዳለበት
ያምናል፡፡ በተጨማሪም በየጊዜው የሰላምና ደኅንነት ፍላጎት
ዳሰሳ ጥናቶች ላይ በመመስረት የቴክኒክና የቁሳቁስ ድጋፎችን
ያደርጋል፡፡ የስልጠና ፍላጎት የምናረካባቸው ሂደቶች
ለመመረጅና ለመሰለል በማያመች መልኩ እንዲከናወኑ
መርሆችን በማዘጋጀት ቅድመ ጥንቃቄ ይደረጋል፡፡የአገር
መከላከያ ሰራዊት አባላት ከቁጥር ይልቅ ፕሮፊሽናል የሆኑና
በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎታቸው የዳበረ እንዲሆን ዘርፈ
ብዙ አቅም የማጎልበት ሥራ የግድ ይሆናል፡፡
መ) የወታደራዊ አታቼዎች እና የሰላም ማስከበር አሰራር
ሁኔታ
አብን የወታደራዊ አታቼዎች የአመዳደብ ሥርዓት በወታደራዊ
የሙያ ብቃትና በአካዳሚዊ አውቀት መሰረት እንዲሆን
በመርህ ላይ የተመሰረተ አሰራርን እውን ያደርጋል፡፡
ንቅናቄያችን በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሰላም ማስከበር
ረገድ በአመራሮች አመዳደ ብግልጽነትና በአሰራሮቹ
ተቋማዊነት ላይ የሚስተዋሉትን ክፍተቶች ለመቅረፍ
204 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !