Page 202 - አብን
P. 202
አብን
ቅራኔና ግጭቶችን በአግባቡ ለመፍታት የሚያስችሉ
አገርአቀፍ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን መንደፍና
ተግባራዊ ማድረግ፤
የዜጎችን ሁለንተናዊ ፍላጎትና ጥቅም በእኩልነት
የሚያስተናግድ ጠንካራ አስተዳደራዊ ሥርዓትን መፍጠር፤
ለሰላምና ደኅንነት ብሎም ለሕግ የበላይነት መከበር
አይነተኛ ሚና የሚጫወቱትን የአገር መከላከያ፣ የፖሊስና
የፍትኅ ተቋማትን ከፖለቲካ ወገንተኝነት በፀዳ ሳይንሳዊና
ሕጋዊ መስመር እንዲዋቀሩና ሕዝባዊ አመኔታ
የሚጣልባቸው ተቋማት እንዲሆኑ በፖሊሲ ማእቀፍ
የታገዘ የድጋፍና ክትትል ተግባራትን መከወን፤
የሕግ የበላይነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ማስከበር፤
ሥራ አጥነትን በመቀነስ ወጣቱ ኃይል በሰላምና ደኅንነት
ግንባታው ላይ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ማስቻል፤
የሴቶችን ተሳትፎ በማሳደግ በሰላምና በሁለንተናዊ ዘርፉ
የጎላ ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችል የፖሊስ ማእቀፍን
መተግበር፤
የውጭ አገር ግንኙነቶችን ለአገር ሰላምና ደኅንነት ስጋት
በማይሆኑበት የፖሊሲ ማእቀፍ መምራትና ሂደቶችንም
መገምገም የሚያስችል ጥናትና ስትራቴጂን መከተል፡፡
አገር በቀልና የውጭ አገር የሲቪክና የበጎ አድራጎት
ማኅበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት ብሎም የአገር
ሽማግሌዎች በሰላምና ደኅንነት ረገድ ጉልህ ሚና
የሚጫወቱበትን የአሰራርና የፖሊሲ ማእቀፍ መዘርጋት
ናቸው፡፡
200 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !