Page 212 - አብን
P. 212

አብን


             ጋር በመናበብና በመደጋገፍ የመስራት ዲፕሎማሲ እንዲሁም

             የኤክስትራዴሽን ውሎችን ማስፋትም ታሳቢ ይደረጋል፡፡

             4.3 የውጭ ጉዳይ

             አብን  በደኅንነትና  የውጭ  ጉዳይ  ፖሊሲ  በሚከተሉት  ቁልፍ
             ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡

                    1.  በኢትዮጵያዊያን  የተባበረ  ክንድ  ታፍሮና  ተከብሮ

                        የኖረውን  የኢትዮጲያን  ሉዓላዊነትና  ብሔራዊ
                        ጥቅሞች  ማስጠበቅና  አገራዊ  ከብሯን  መመለስ፤
                        ይህም  ማለት  ታሪክ  ተገቢው  ክብር  ተሰጥቶት
                        ውስጣዊ       ሁኔታዎች          በውጭ       ተጽዕኖ       ስር
                        እንዳይወድቁ  የማድረግና  የመጠበቅ  ተግባር  ላይ
                        ማተኮር፣

                    2.  በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን ደህኅነት፣ ነጻነትና
                        ክብርን  ማስጠበቅ፤  ኢትዮጲያዊያን  በሚኖሩበት
                        አገር  ሕጋዊ  እውቅና  አግኝተው  ኃላፊነታቸውን
                        በአግባቡ           እየተወጡ              መብቶቻቸውንና
                        ጥቅሞቻቸውንም  የማስከበር  ግዴታን  በአግባቡ
                        መወጣት፣
                    3.  ኢትዮጲያ  የባሕር  በር  የማገኝት  መብቷን  እውን
                        ማድረግና        ደኅንነቱ      የተጠበቀ        የባሕር      በር

                        አገልግሎት  (maritime  service)  እንዲኖር  መርኃ
                        ግብር አዘጋጅቶ መስራት፤




             210    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   207   208   209   210   211   212   213   214   215   216   217