Page 217 - አብን
P. 217

አብን


                        of  democratic  over-sight)  እንዲቃኙ  የማድረግ

                        ሥራ ይሰራል፡፡

             4.3.1 የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ መርሆች፣ ግብና ዓላማዎች

             ሀ) የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ መርሆች
             የኢትዮጵያ  የውጪ  ግንኙነት  ፖሊሲ  ጤናማና  ውጤታማ
             የሚሆነው የዓለም አቀፍንና የአገር ውስጥ ቁልፍ ሁኔታዎችን
             የሚመለከት  ጥልቅ  ትንተናን  መሰረት  ያደረገ  የብሔራዊ

             ጥቅም  ማስፈጸሚያ  መርሆች  ሲኖሩት  ብቻ  እንደሆነ  አብን
             በጽኑ  ያምናል፡፡  የፖሊሲ  መርሆች  የተሳካ  ግንኙነት
             ለማድረግ  የሚያግዙ  የግንኙነት  ሂደቶች  መቃኛዎች  ናችው፡፡
             አብንም  ከዚህ  አተያይ    በመነሳትና  ከሁኔታዎች  ጋር
             የተጣጣመ የውጭ ፖሊሲ መርኅ ማሻሸያ እንደሚኖር ታሳቢ
             በማድረግ ከታች የተዘረዘሩ መርሆችን አስቀምጧል (በቀጣይም

             መርሆቹ  ተፈጻሚ  የሚሆኑባቸውን  ስልትና  ስትራቴጂ
             ይነደፋል)፡፡
                  የኢትዮጵያን  ሕዝብ  ዘላቂ  ጥቅም  ማሰከበርና  በጋራ
                    መተማመን  ላይ  የሚመሰረት  የውጭ  ግንኙነት  እውን
                    ማድረግና ማስቀጠል፤
                  የኢትዮጵያን  ሕዝብ  ሁሉንአቀፍ  ዘላቂ  ጥቅምና
                    የወደፊት         እጣፋንታ         የማይጸረሩ          ዓለምአቀፍ
                    ስምምነቶችን  መፈራረም፣  ሕግና  ደንቦችን  መጠበቅና

                    መተግበር፤
                  በሌሎች  አገራት  የውስጥ  ጉዳይ  ጣልቃ  ያለመግባት
                    መርኅ  እንደተጠበቀ  ሆኖ  በቀጥታም  ሆነ  በተዘዋዋሪ


             215    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   212   213   214   215   216   217   218   219   220   221   222