Page 219 - አብን
P. 219
አብን
ብሔራዊ ጥቅም የማስጠበቅና ለዜጎች አመች የሆነች አገር
እውን የማደረግ ግብን የሰነቀ ነው፡፡
ሐ) የውጭ ግንኙነት ዓላማ
አብን የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስከበር የሚደረገውን
ሰላማዊ ትግል ውጤታማ ለማድረግ የሚከተሉትን የውጭ
ፖሊሲ ዓላማዎች አስቀምጧል፦
በዓለምአቀፍ ደረጃ ያሉ የፖለቲካ፣ የሕግ፣
የማኅበራዊና ወዘተ መስተጋብሮች የኢትዮጵያን ጥቅም
የሚያከብሩ እንዲሆኑ ማስቻል፣
በተለያየ ዓለም የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዜጎችና ትውልደ
ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ ሁሉአቀፍ ልማት ውስጥ
ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ፤
አገሪቱ የፈረመቻቸው የዓለምአቀፍ ሕጎችን በመጻረር
በፖለቲካዊ ውሳኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ
የተፈጸሙትን ግፎች በማስረጃ አስደግፎ ለዓለምአቀፉ
ማኅበረሰብ ማስገንዘብና ለተፈጸመው ግፍ በሽግግር
ፍትኅ (transitional justice) እንዲካስ ማስቻል፤
የዓለምአቀፍ ሕጎች የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብሩ
መሆናቸውን ማረጋገጥ፤እንዲሁም ዓለምአቀፍ
ውሎችና ስምምነቶች እንደየሁኔታው እንዲጸድቁ
ወይም እንዳይጸድቁ ሙያዊ አስተያየት በማቅረብ ንቁ
ተዋናይ መሆን፤
217 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !