Page 223 - አብን
P. 223

አብን




             መ)  በአገር  ውስጥ  ባሉ  የውጭ  አገር  ተቋማትንና
             ኢምባሲዎችን መጠቀም

             በታሪክ  አጋጣሚ  ኢትዮጵያ  የዓለም  ተቋማት  በብዛት
             ከሚገኝባቸው ጥቂት የዓለም አገራት መካከል አንዷ ናት፡፡ ይህ
             አይነት  አጋጣሚ  በአገሪቱ  የሚደረጉ  ለውጦችንና  በኢትዮጵያ
             ላይ ያላቸውን ሁለንተናዊ እንድምታ ለመስገንዘብ፣ የኢትዮጵያ
             ሕዝብ ጥቅም የሚያስጠብቅ ድርድር ለማድረግ አመች ሁኔታ

             የሚፈጥር         ነው፡፡     በመሆኑም          አብን      የሚመሰርተው
             ከዓለምአቀፉ  ማኅበረሰብ  ጋር  የሚኖረውን  የዲፕሎማሲ  ሥራ
             በእነዚህ  ተቋማት  አማካኝነት  ይሰራል፡፡  ኢምባሲዎችም
             የየአገራትን  መልዕክተኞችና  አምባሳደሮች  በቅርብት  ማግኘት
             ስለሚያስችሉ  እነሱ  በሚያደርጉት  ጥሪና  በራስ  ተነሳሽነት
             ማብራሪያ  በመስጠትና  በመቀበል፣  ውትወታ  በማድረግና

             በማግባባት  የኢትዮጵያን  ሕዝብ  የኅልውና  ትግል  የሚጠቅም
             የግንኙነት       ሥራ       ይሰራል፡፡      ኢምባሲዎችንና           ወኪሎች
             በመጥራት  እና  ወደ  እነሱም  በመሄድ  ከዲፕሎማሲው
             ማኅበረሰብ አይንና ጆሮ ሳይደርስ የሚቀረውን የአገርን ጥቅም
             የሚያስከብር የኮሙኒኬሽን ሥራ ይከወናል፡፡

             ሰ) የመከላከያ ኃይል ትግበራ


             ኢትዮጲያ ከውጭ ወረራና ትንኮሳ ስጋት ለመዳን የራሷ የሆነ
             ጠንካራ  መከላከያ  ኃይል  መገንባት  ያስፈልጋታል፡፡  ይህም
             ተጋላጭነትን  የመቀነስ  ወይም  ሌላው  አካል  እዳይዳፈር


             221    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   218   219   220   221   222   223   224   225   226   227   228