Page 226 - አብን
P. 226
አብን
የወደብ ባለቤትነት ካረጋገጠ ከ41 አመታት በኋላ በ1983
ዓ.ም. የተከሰተው የኢህአዴግ የፖለቲካ ሥርዓት አገሪቱን
በአፍሪካ ትልቋ ወደብ አልባ ወይም ምድር ዘግ አገር
አድርጓታል፡፡ በኢትዮጵያ የውጭ ፖሊሲ ቅርጽና ይዘት ላይ
ከፍተኛ ለውጥ አስከትሏል፡፡
የባሕር በር ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር ፖለቲካዊና
ወታደራዊ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡ አብን የወደብ አገልግሎት
እንደ ሆቴል አገልግሎት በኪራይ ከመጠቀም ጋር አመሳስሎ
በማሰብ የውጭ ፖሊሲን ለመቅረጽ መሞከር ስህተት ነው
የሚል አቋም አለው፡፡ ወደብ አልባ አገራት በዓለምአቀፍ ሕግ
መሰረት የወደብ አገልግሎት መብት እንደሚኖራቸው የተደነገገ
ቢሆንም የባሕር ጠረፍ ያላቸው አገራት የሉዓላዊነት መብት
ወደብ-አልባ አገራት የሚያገኙት አገልግሎት ከባለጠረፍ
አገራት በሚያደርጉት ድርድር የሚወሰን ነው፡፡
አብን ወደብ አልባነት የኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀንድ አንጻራዊ
ገናናነት የሚገድብ መሆኑን በማጤን ሌሎች የአገሪቱን
ጸጋዎች በአግባቡ በመጠቀም ወደብ አልባነቷ የሸረሸረባትን
የመደራደር አቅም ማካካስና የፖለቲካ ኢኮኖሚ ኃይልን
ተገዳዳሪ ማድረግ ይቻላል ብሎ ያምናል፡፡ የኢትዮጵያን
የባሕር-በር አጠቃቀም የሚመለከት የፖለቲካ አቅጣጫ
በአፍሪካ ቀንድ ወደቦች ልማትና አስተዳደር ረገድ እያደገ
ያለውን የባሕረ ሰላጤውን አገራት ተሳትፎ እድልና ስጋቶች
ከግምት ያስገባ እንዲሆን አስገዳጅ ሁኔታዎች አሉ፡፡
224 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !