Page 231 - አብን
P. 231
አብን
ከምርጫ በኋላ የትኛውም ወቅቱ በሚጠይቀው የትብብር
መስክ ከሌሎች ኃይሎች ጋር በመሆን ከላይ ከተዘረዘሩ
ከዲያስፖራ ባለሃብቶች ጋር የተያያዙ ተግባራትን በማካናወን
የአገሪቱን እድገት ለማፋጠን ይሰራል፡፡
4.4.2 የዲያስፖራ ምሁራን
ከ1983 ዓ.ም. ወዲህም ሆነ ከዚያ በፊት በፖለቲካው
ጎራባጭነት የተነሳ ወይም የተሻለ ሥራና ክፍያ ፍለጋ በሽህ
የሚቆጠሩ ምሁራን ወደ ውጭ አገር በመሄድ እዚያው
እንደሚኖሩ ይታወቃል፡፡ ተራማጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ምሁራን
በዝቅተኛ ደረጃ ባሉ የመንግስት ቢሮ ክራሲዎች ውስጥ
ከመቀጠር ያለፈ እድል እንደማይኖረቸው የሚያስረዱ ብዙ
የሰነድ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ምሁራን የአገሪቱን
መለወጥ የሚደግፉ እና የቻሉትን እንደሚያደርጉ የሚታወቅ
ነው፡፡ የምሁራኑ ሚና የትየለሌ ሲሆን ከነዚህም የአገሪቱን
ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች ተችቶ የማጠናከር፣ ሙያን
የማካፈልና የልምድ ልውውጥ ማድረግ፣ እንደ ዲፕሎማት
ማገልገል የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በተጨማሪ
ምሁራኖቹ ሊወጡ የሚገባቸውን ዘርፈ ብዙ ሚና እንዲወጡ
የውጭ ጉዳይ/ሚኒስቴር/ ክፍል በመቀስቀስ መርኅ ተግባር
በማዘጋጀትና ግንኙነት በመፍጠር ተነሳሽነቱን ይወስዳል፡፡
4.4.3 በውጭ አገር ተወልደው እዚያው የሚኖሩ ትውልደ
ኢትዮጵያውያን
229 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !