Page 230 - አብን
P. 230
አብን
ኢትዮጵያዊያን፣ የዲያስፖራ ምሁራን፣ በውጭ አገር
ተመስርተው እየተንቀሳቀሱ ያሉ የተለያዩ ድርጅቶች በሚሉ
ንዑስ ክፍሎች አብን የፖሊሲ አቅጣጫዎች ተወስተዋል፡፡
4.4.1 የዲያስፖራ ባለኃብቶች
በሚሊዮን የሚቆጠር የኢትዮጵያ ሕዝብ በውጭው ዓለም
ይኖራል፡፡ በተለይ በምዕራቡ ዓለም በአሜሪካ እና በአውሮፓ
ከፍ ያለ ቁጥር ያለው ኢትዮጵዊ እንዳለ ይታወቃል፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ እና በአፍሪካ አገራት በርካታ
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም፡፡
በመሆኑም በአገሪቱ የኢኮኖሚና ተያያዥ የእድገት ሂደቶች
ውስጥ እምቅ ኃይል በመሆኑ ጥቅም ላይ ማዋልና የማንነቱ
መገለጫ በሆነችው አገሩ ኃብት አፍርቶ በነጻነት እንዲኖር
የማስቻሉ ሥራ አብይ ትኩረት ይቸረዋል፡፡ በውጪ የሚገኙ
ባለሃብቶች እራሳቸውንና አገሬውን በአጭርና በረጅም ጊዜ
ሊጠቅሙ የሚችሉ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ
ማበረታታት ትኩረት የሚሻ ሆኖ ባለሃብቱ ከምሁራን ጋር
ሆነው ልማዳቸውን በመቀመር አገሪቱን ለማልማት አጋዥ
የሆኑ እቅዶችን በማዘጋጀት፤ አቅጣጫዎችን በማሳየት
መሳተፋቸው አስፈላጊ በመሆኑ አብን ኃላፊነቱን ወስዶ
ሂደቱንና ፍጻሚውን ያመቻቻል፡፡በዚህም ውስጥ ዲያስፖራው
የጥሪትና የኃብት ባለቤት በሚያደርጉ የአክሲዮን ገበያዎች፣
በግብርና ኢንቨስትመንት፣ በአዋጭና ቀጣይነት ባላቸው
የኢንዱስትሪ ሥራዎች ወዘተ… ተሳታፊ ባለኃብቶችን መሳብ፣
መፍጠር እና በማልማት ሥራ ላይ ትኩረት አድርጉ ይሰራል፡፡
228 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !