Page 229 - አብን
P. 229
አብን
በተጨማሪም አብን የኤክስክሉሲቭ ኢኮኖሚክዞን (Exclusive
Economic Zones) እና የዓለምአቀፍ ውኃን (High Sea)
መጠቀም የሚስችሉ የዓለምአቀፍ ስምምነቶች የሁሉንም
ሕዝብ ተሳትፎ፣ ውክልናና የወደፊት ሁሉ-አቀፍ
ብልጽግናውን የሚያረጋግጡ እንዲሆኑ ይሰራል፡፡ የሕዝብ
ቁጥር መጨመርና የኢኮኖሚ ማደግ የባሕር ላይ ንግድ
እንዲያሻቅብ ስለሚያደርግና የባሕር ላይ እንቅስቃሴውን በራስ
አቅም ለመጠበቅ ብሎም ዘመኑ በሚጠይቀው አግባብ የአገር
ጸጥታን ለመጠበቅ የባሕር ኃይል ማደራጃት እንደሚያስፈልግ
ይታመናል፡፡ በመሆኑም የባሕር በር ካላቸው የአፍሪካ ቀንድ
አገራት ጋር የሁለትዮሽና ከዚም ከፍ ያለ ድርድር በማድረግ
ኢትዮጵያ በክልሉ አወንታዊ ተገዳዳሪ አገር እንድትሆን
ለማስቻል የሚሰራ ይሆናል፡፡
4.4 የዲያስፖራ ማኅበረሰብ እና ተቋማት ጉዳይ
የአብን ድያስፖራ ተኮር ፖሊሲ የዲያስፖራውን ማኅበረሰብ
የአገራዊ ልማት አካል የማድረግ፣ አዳዲስ የዲያስፖራውንና
የትውል አገሩን/ኢትዮጵያን/ የሚጠቅሙ የልማት እቅዶችን
ነድፎ ዲያስፖራው ተሳታፊ እንዲሆን የማስተባበርና የማገዝ
ሥራ እና እነዚሁ አካላት በሚኖሩባቸው አገራት መብቶቻቸው
እንዲጠበቁላቸው የሚደረገውን ድርጅታዊ መርኅ የሚመለከት
ነው፡፡ በዚህ ሰነድ ላይ ለሚደረገው ገለጻ አመችነት ሲባል
የዲያስፖራውን ማኅበረሰብ በዘርፍና በአደረጃጀት በመከፋፈል
መዳሰሱ ተመራጭ ነው። በመሆኑም የዲያስፖራ ባለሃብቶች፣
በውጭ አገር ተወልደው እዚያው ያደጉ ትውልደ
227 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !