Page 234 - አብን
P. 234
አብን
መርህ 1፡ አሃድነት/ውህደት (Unity) ፡- በአገሪቱ
የሚደረጉ ሁሉአቀፍ እድገት በበውህደት መስራት
የመጃመሪያ ምርጫ በመሆኑ ሁሉም ድርጅቶች
ይህኛውን መስመር እንዲከተሉ ይበረታታል፡፡
መርህ 2፡ ሕብረት መፍጠር ወይም መቀናጀት
(coalition)
መርህ 3፡ትብብር ወይም መተጋገዝ (cooperation)
መርህ 4፡ ያለመገፋፋት፦ (በሚያስማሙ ጉዳዮች ላይ
አብሮ መስራት በማያስማሙ ጉዳዮች ላይ
ባለመገፈታተር አገራዊ ስዕሉ ላይ የሚኖረው የጋራ
እሴትን የትስስር እትብት አድርጎ መቀበል (using the
big picture, the common national value as a
bond).
በአጠቃላይ በውጭው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን
እንደግለሰብ፤ ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊን የመሰረቷቸው ተቋማት
ለኢትዮጵያ ሁሉአቀፍ እድገት እንዲያበረክቱ የሚደረገው
ጥረት እንዳለ ሆኖ እነዚሁ አካላት በአበርክቷቸው ልክ
በፍትኃዊነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረጉ ሥራ እና
ከትውልድ አገራቸው ጠንካራ የማኅበረ-ኢኮኖሚ ትስስር
የመፍጠሩ ጥረት ተቀዳሚ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡
በተጨማሪም የዲያስፖራው ማኅበረሰብ አባላትና
ድርጅቶቻቸው በሚኖሩባቸው/ባሉባቸው/ አገራት መብታቸው
በተሟላ መልኩ እንዲጠበቅ ጠንካራ የዓለምአቀፍ ሕጎችን
መሰረት ያደረጉ የዲፒሎማሲ ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡
232 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !