Page 233 - አብን
P. 233

አብን


             ደርጅቶችና  ሚዲያዎች  በውጭ  እንዳሉ  ይታወቃል፡፡  በዚህ

             ውስጥ ሰብዓዊ መብትና የዲሞክራሲ፣ የፖሊተካ፣ የኢኮኖሚ፣
             የማኅበራዊ፣  የሙያ  ባሕልና  ወዘተ…  ድርጅቶች  ይካተታሉ፡፡
             አብን በውጭ አገር ያሉ በኢትዮጵያዊያን የተቋቋሙ ልዩ ልዩ
             ደርጅቶች በዘርፈ ብዙ አጋርነት እንዲሳተፉ ወይም አገልግሎት
             እንዲሰጡ  የአሰራር  መርሆችን  በማዘጋጀት  አበርክቷቸው
             ውጤታማ  እንዲሆን  ይሰራል፡፡  የሚዲያ  ተቋማት  የገጽታ
             ግንባታና  ፐብሊክዲፕሎማሲ  አስተዋጾ  ድርሻ  እንዲኖራቸው፣
             እንዲሁም  የመረጃ  አድራሽነትና  አቀባይነት  ሚናን  በመወጣት

             ሕዝቡን  ለማንቃት  በሚያስችል  መልኩ  ዝርዝር  መርኃ-ግብር
             ተነድፎ  ይተገበራል፡፡  ሁሉም  አይነት  ተቋማት  የኢትዮጵያን
             አንድነት  የሚያናጉ  የመንግስት  እና  መንግስታዊ  ያልሆኑ
             ተቋማትን ድርጊት ለማረም፣ በአማራ እና በሌላው ሕዝብ ላይ
             የተፈጸመውንና  እየተፈጸመ  ያለውን  ግፍ  በማስረጃ  አስደግፎ
             ለመታገል  እና  ከ50  ዓመታት  በላይ  እድሜ  ያስቆጠረውን

             የተዛባ  /አገር  አፍራሽ/  ትርክት  ለመቀልበስ  ሁነኛ  ጉልበት
             ናቸው፡፡ሆኖም  ጥቃቅን  ልዩነቶች  የወለዷቸው  የጎንዮሽ
             መጎነታተልና  የጠነከረ  ኅብረት  የመፍጠር፣መዋሃድ  ወይም
             የጋራ  ግንባር  መመስረት  ክፍተቶች  ይታያሉ፡፡  እነዚህን
             ተቋማት ወደ አንድ በማምጣት ኃይል እንዳይበታተን ማድረግ
             ይቻላል፡፡       በመሆኑም         የአብን       በውጭ        አገር      ያሉ
             የኢትዮጵያዊያን          ተቋማት        በሚከተሉት         መርሆች        ላይ
             የተመሰረተ  የትግል  ሥልት  እንዲከተሉ  የአስተባባሪነት  እና

             የአማቻችነት ሚና ይኖረዋል፡፡





             231    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   228   229   230   231   232   233   234   235   236   237   238