Page 232 - አብን
P. 232

አብን


             በውጭ  አገራት  ተወልደው  እዚያው  የሚያድጉ  ወገኖች

             የሚኖሩበትን  አገር  ማኅበራዊ  ሥሪት  ይይዛሉ፡፡  ከኢትዮጵያዊ
             ባሕል፣  ወግና  አኗኗር  የራቁ  በመሆኑ  በአጭር  ጊዜ  የአገራዊ
             እሴቶችን  አላብሶ  ከአገር  ቤቱ  ጋር  የሥነ-ልቦና  ትስስር
             መፍጠር  ያዳግታል፡፡  ሆኖም  ሕጻናት፣  ልጆችና  ወጣቶች
             በኢትዮጵያዊ  ሥነ-ልቦና  ተኮትኩተው  እንዲያድጉ  ቤተሰብ፣
             የኃይማኖት አባቶች፣ የሲቪክ ተቋማትና መንግስት ሚናቸውን
             እንዲወጡ  ፕላትፎረሞችን  በመዘርጋት  የተፈለገውን  ውጤት
             ለማምጣት ይሰራል፡፡

             በሙዚቃ፣ በሥነ-ጽሁፍ እና በመደበኛ/ኢ-መደበኛ ትምህርቶች
             አገራዊ እሴቶችን እንዲያውቁ ማደረግ (ባሕል፣ ሥነ-ምግባር፣
             ታሪክ፣  የቋንቋ፣  ወዘተ)   እና  ይህንንም  አብን አገር  ውስጥና
             ውጭ  ካሉ  የሙያና  የባሕል  አደረጃጀቶች  ጋር  በመተባበር
             የሚተገብረው ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ወደ አገር ቤት ጉብኝት
             እንዲያደርጉ  እና  ከአገራዊ  እሴት  ጋር  እንዲተዋወቁ

             የማበረታታት          ሥራም         ይሰራል፡፡       አቅም       በፈቀድም
             የኢትዮጵያን         ኅብረብሔራዊ          እሴቶች       የሚንጸባረቅባቸው
             የኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤቶች በውጭ አገራት እንደመሰረቱ እና
             የተመሰረቱትም  እሴቶች  ከአካዳሚው  በተጓዳኝም  ቢሆን
             በተጠናከረ  መልኩ  የኢትዮጵያ  ሕዝብ  እሴቶችና  ታሪክ
             እንዲያስገነዝቡ ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር ይሰራል።
             4.4.4  በውጭ  አገር  ተመስርተው  እየተንቀሳቀሱ  ያሉ
             ድርጅቶች


             በአሁኑ  ሰዓት  በቁጥር  የምናውቃቸው  የኢትዮጵያን  ጉዳይ
             ጉዳቸው  አድርገው  የሚሰሩ  የኢትዮጵያዊን  ልዩ  ልዩ


             230    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   227   228   229   230   231   232   233   234   235   236   237