Page 236 - አብን
P. 236

አብን


             የአገሪቱ  ዳር  ድንበር  እና  ሉዓላዊነት  አስተማማኝ  ሁኔታ

             እዲጠበቅና  እንዲከበር፣  ሐሰተኛ  የታሪክ  ትርክትን  መሰረት
             ያደረገ ፖለቲካ በሚገባ ተጋልጦ በምትኩ በእውነተኛ የአገሪቱ
             ታሪክ ላይ በተገነባ የዲሞክራሲያዊ ፓለቲካ እንዲተካ፣ በመላ
             አገሪቱ ሰላም እንዲሰፍንና  የተሻለ  የማኅበረሰቦች  የእርስ በርስ
             ግንኙነት እንዲኖር ለማድረግ የሚሰጠ ውሳኔ ነው፡፡


             አብንን  መምረጥ  በመንጋ  ሕግ  ምትክ  የሕግ  የበላይነት
             የሰፈነበት፣  የኃሳብ  ነጻነት  እና  ተቃዉሞ  በሰላማዊ  መንገድ
             የመግለጽ        መብት         የሚከበርበት፣          ዜጎች       በፖለቲካ
             አመለካከታቸዉ           ምክንያት        አለአግባብ        ከሕግ       ዉጭ
             የማይታሰሩበት፣  የጎሳ  ፖለቲካ  በዜግነት  ፖለቲካ  የሚተካበት
             ሁኔታ እንዲፈጠር የማድረግ ቁርጠኛ ውሳኔ ነው፡፡


             አብንን  መምረጥ  በኢትዮጵያ  ውስጥ  ዳግመኛ  የዘር  ማጥፋት
             ወንጀል  እንዳይፈፀም፣  እስካሁን  የተፈፀመውም  ወንጀልም
             በገለልተኛ  አካል  ተጠርቶ  አጥፊዎች  ለሕግ  የሚቀርቡበት፣
             አጥፊዎች  ጥፋታችውን  በይፋ  የሚናዘዙበት፣  በዚህም  ሂደት
             አገራችን ወደ ብሔራዊ እርቅ እንድታመራ ለማድረግ የሚሰጥ
             ውሳኔ ነው፡፡


             አብንን  መምረጥ  ግልፅነት  ባለው  የገበያ  ኢኮኖሚ  መርሆዎች
             የሚመራ፣  የመሬት  የግል  ባለቤትነት  መብት  የሚከበርበት፣
             አብዛኛው  የኢኮኖሚ  እንቅስቃሴ  በግሉ  ዘርፍ  የሚከናወንበት፤
             መንግስት  በኢኮኖሚው  ውስጥ  የሚኖረው  ሚና  በመሰረተ
             ልማት  ግንባታ፣  የግሉ  ዘርፍ  በአቅም  ውስንነት  ምክንያት
             ሊገባባቸው        ባልቻሉ        ትላልቅ       የኢኮኖሚ         አውታሮች
             መዋዕለነዋዩን በማዋል እና በተለይም በኢኮኖሚ ቁጥጥር እና

             234    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   231   232   233   234   235   236   237   238   239