Page 235 - አብን
P. 235
አብን
ክፍል 3
ማጠቃለያ
1. የማኒፌስቶው አፈፃፀም እና የመራጩ ውሳኔ
አብን በመጭው ግንቦት - ሰኔ ወራት 2013 ይካሄዳል
በተባለው ምርጫ የመራጩን ሕዝብ አብላጫ ድምጽ ካገኘ፣
ስልጣን በያዘ በ100 ቀናት ጊዜ ውስጥ በዚህ ለምርጫ
በቀረበው ማኒፌስቶ ወይም መርኃ ግብር ውስጥ ዘርዝሮ
ያቀረባቸው አብይ ጉዳዮችን አፈፃፀም በተመለከተ ለመራጩ
ሕዝብ ዝርዝር የአፈፃፀም ሪፖርት ያቀርባል፡፡ ከዚያም
የየዓመት የክንውን ሪፖርት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያቀርባል፡፡
አብን ቀደም ሲል በትሕነግ /ኢህአዴግ የሃያ ሰባት ዓመት
የሥልጣን ዘመን፣ አሁንም በቅርቡ ደግሞ በኦሮሞ ብልፅግና
ያለፉት ሦስት ዓመታት የሥልጣን ቆይታ እና ገዥ ፓርቲው
በሚከተለው የተረኝነት ፖለቲካ የኢትጵያ ሕዝብ የደረሰበትን
አስከፊ የመከራ እና የሰቆቃ ሁኔታ በጥልቅ ይገነዘባል፡፡ አብንን
መምረጥ ኢትዮጵያን ከአገዛዝ ወደ ዲሞክራሲ ለማሸጋገር፣
ጽንፈኛ ብሔርተኞች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫኑበትን ሕገ-
መንግሥት እዲለወጥ፣ በቋንቋ ላይ ብቻ የተመሰረተው
‘ፌደራሊዝም’ ተሽሮ በምትኩ የሁሉንም ዜጎች መብት እና
ጥቅም የሚያስከብር እውነተኛ የፌደራሊዝም ሥርዓት
እንዲገነባ መወሰን ነው፡፡
233 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !