Page 237 - አብን
P. 237
አብን
ክትትል ተግባር ላይ ብቻ የሚወሰንበት ውሳኔ ነው፡፡ በዚህም
ዓይነት የልማት ሞዴል አማካይነት በአገሪቱ የተንሰራፋውን
ድህነት በአጭር ጊዜ ውስጥ አስወግዶ ለዘላቂ ልማት
አስፈላጊው የመወንጨፊያ መሰረት የሚጣልበትን ሁኔታ
ለማየት የመቁረጥ ውሳኔ ነው፡፡
2. አገራዊ ጥሪ
2.1 .በኢትዮጵያውን አጠቃላይ በተለይም በአማራ እና ሌሎች
ወንድም ሕዝቦች ላይ የተጫነውን መዋቅራዊና ሥርዓታዊ
ጭቆና ለመገርሰስ አብንንይምረጡ፤
2.2 ኢትዮጵያን ከአገዛዝ ሥርዓት ወደ ዲሞክራሲ ለማሸጋገር
አብንን ይምረጡ፤
2.3 በሥራ ላይ ያለውን ለኢትዮጵያ አንድነት ፀር የሆነው
ሕገ-መንግስት እንዲሁም የቋንቋ ፊደራሊዝም መንግስታዊ
አወቃቀር እንዲቀየር ለማድረግ አብንን ይምረጡ፤
2.4 በኢትዮጵያ ውስጥ ደግመኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል
እንዳይፈፀም፣ የእርስ በርስ ግጭትና ደም መፋሰስ
እንዳይከሰት የምትፈልጉ አብንን ይምረጡ፤
2.5 ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ሰፍኖ የቆየውን መንግሥት መር
ተቋማዊ ሙስና እዲወገድ፣ ፖለቲካን ወደ ኢኮኖሚያዊ
ካፒታል መቀየር ቋሚ ተግባሩ ያደረገ መንግሥታዊ
አሰራር እንዳይኖር ለማድረግ፣ ማለትም እንደ ሕገ-ወጥ
የመሬት ወራሪ እና የኮንዶሚኒየም ቤቶች ንጥቂያና
ዝርፊያ ተወግዶ፣ በዚህ ሕገ-ወጥ ተግባር የተሰማሩ
ባለሥልጣኖች በሕግ ፊት እንዲቀርቡ እና ያለ አግባብ
በሕገ-ወጥ መንገድ ያገኙት ኃብት ተመልሶ የኃብት
235 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !