Page 227 - አብን
P. 227
አብን
ባለፉት 30 ዓመታት የኢትዮጵያ ጉሮሮና የውጭ የመፈናፈኛ
መስመር ሆና ስታገለግል የነበረችው የጅቡቲ ዋነኞቹ ወደቦች
በሶስተኛ ወገን ቁጥጥር ሥር መሆናቸው የአገራችንን
ሁለንተናዊ አቅምና የወጭ-ገቢ እንቅስቃሴ ለባዕድ/ተቀናቃኝ/
አካላት ቁጥጥርና ለስለላ የሚያጋልጥ ነበር፡፡ ሁኔታው በጋራ
ጥቅም መርኅ ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የኢትዮጵያ
ተጋላጭነት ከኢኮኖሚ ባሻገር ሆኖ ቆይቷል፡፡
ዛሬ ላይ የኤርትራ ወደብ ለኢትዮጵያ ክፍት መደረጉ፣ የሶማሊ
አንጻራዊ መረጋጋት፣ የኬንያና የሱዳንም ወደቦች
በአማራጭነት መኖራቸውን እንደመልካም አጋጣሚ መውሰድ
ይቻላል፡፡ ይህም የአገሪቱን የውጭ ንግድና ተያያዥ
እንቅስቃሴ ከአንድ አገር ጥገኝነት በማላቀቅ በተለያዩ አገራት
ወደብ ለመጠቀም እድል ይሰጣል፡፡ ከብዙዎቹ የአፍሪካ ቀንድ
አገራት ጋር መሰል ግንኙነት መፍጠሩ አገራቱን ወደ ተሻለ
የኮንፌደሬሽን አወቃቀር የመጋበዝ እድል ስላለው ከወደብ
አገልግሎት በተጨማሪ ዘርፈ ብዙ ድንበር-ዘለል የመሰረተ
ልማት ዝርጋታዎችን ማከናወን ያስፈልጋል፡፡
የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ የፖሊሲ አቅጣጫ
በመሆኑም ኢትዮጵያ በአጭርና በመካከለኛ የእቅድ ዘመን
እኤአ የ1982 የባሕር ሕግ በሚፈቅደውና ከባለወደብ አገራት
ጋር በሚደረግ ስምምነት ብሎም አገልግሎት አቅራቢ አገራትን
በማጠናከር/ በማስፋት የባሕር በር አልባነት የፈጠረባትን
ተጋላጭነቷን ልትቀንስ ትችላለች፡፡ በተጨማሪ በተለያዩ
225 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !