Page 228 - አብን
P. 228
አብን
የአገራችን አካባቢዎች በተለይም በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን፣
በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምስራቅ፣ በደቡብና
በማዕከላዊ ኢትዮጰያ የደረቅ ወደብ ተቋማትን በመገንባት
የሱዳንን ወደብ (Port Sudan)፣ የኤርትራን ወደብ (አሰብን-
Asab)፣ የጂቡቲን ወደብ (Djibouti port)፣የከፊል ራስ ገዝ
ሶማሊላንድን ወደብ (Berbera) እና የኬንያን ወደብ
(Mombassa) ለደረቅ ወደቦቹ እንደሚኖራቸው ቀረቤታና
አመችነት አማራጭን የማስፋት ሥራ መተግበር ያስፈልጋል፡፡
የረጅም ጊዜ የፖሊሲ አቅጣጫ
በረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ የወደብ አገልግሎት በጋራ ገበያ፣
በጋራ ኢኮኖሚና ዘርፈ ብዙ ክልላዊ ትብብሮች ማዕቀፍ ውስጥ
የሚስተናገድበት አግባብ እንዲኖር አብን ይሰራል (ከታች
በሰፊው ተብራርቷል)፡፡ በአፍሪካ ቀንድ የጋራ የጉሙሩክ
ሥርዓት፣ የጋራ ገበያና የጋራ ኢኮኖሚ (custom union,
common marke and common economy) ሂደታቸውን
ጠብቀው እውን የሚያደርግ አገራዊ የፖለቲካ-ኢኮኖሚ
መርሆችን በመዘርጋትና ክልላዊ ዲፕሎማሲን በማሳደግ
ከጂኦፓለቲካዊ ተጋላጭነትን የመነጨውን ጫና ማቅለል
ይቻላል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ክልላዊ ኃይልንና ተጠቃሚነትን
የሚያሳደግ የኮንፌደሬሽን ፖለቲካዊ ጥምረት ከኤርትራ፣
ሱዳን፣ ሶማሊያና ጂቡቲ ጋር እውን እንዲሆን ጥረት
ይደረጋል፡፡
226 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !