Page 164 - አብን
P. 164
አብን
የጤና አገልግሎት አሰጣጥ
የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሲባል በቅድሚያ የጤና
አግልግሎቱ የሚሰጥበትን ተቋማዊ አወቃቅር የሚያመለክት
ሲሆን ከዚህ አንፃርም ተቋማዊ መዋቅሩ በዋናነት መሰረታዊ
የጤና አገልግሎት (primary health care) መሰረት አድርጎ
ይዋቀራል፡፡ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት በቀዳሚነት
መከላከልን መሰረት አድርጎ የሚዋቀር ይሁን እንጂ በደረጃው
ሊሰጡ የሚገባቸውን የፈውስና የተሐድሶ የሕክምና
አገልግሎቶችንም እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ ከዚህ አንፃርም
በዋናነት የእናቶችና ሕፃናት ሕክምናና መከላከል፤ተላላፊ
የሆኑና ያልሆኑ ኅመሞች ሕክምና፤ የስነ-ተዋልዶና ስነ-ምግብ
አግልግሎቶች፤ የአእምሮና የፀረ-ዕፅ የጤና አገልግሎቶች፤
የክትትል የጤና አገልግሎቶች በተጨማሪ በዋናነት
የማኅብረሰብ የማንቃት፤የማስተማር እና የማኅብረሰብ
ተሳትፎን የማጎልበት ሥራዎች የሚከወኑበት ይሆናል፡፡
መሰረታዊ የጤና አገልግሎት የጤናው ዘርፍ ዋነኛ
የአገልግሎት መስጫ ሆኖ የሚዋቀር ቢሆንም የሁለተኛና
የሦስተኛ ደረጃ የጤና አገልግሎት መስጫዎችም
የማኅብረሰቡን የሕዝብ ሥርጭትና የጂኦግራፊ አሰፋፍር
ባማከለ መልኩ ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ ይዋቀራሉ፤
ይቋቋማሉ፡፡ በተጨማሪም ሰፔሻላይዝድ ለሆኑ አገልግሎቶች
ስፔሻላይዝድ የጤና ተቋማት እንዲኖሩ ይደረጋል፡፡ በግልና
መንግሰታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚቋቋሙ የጤና ተቋማት
ለጤና አገልግሎት አሰጣጡ አንኳር አጋሮች መሆናቸው
162 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !