Page 163 - አብን
P. 163
አብን
እንዲሆን ተደርጎ ይዋቀራል፡፡ በመሆኑም ቅድሚያ መከላከልን
መርኅ ያደረገ እንዲሁም የፈውስ፣ ፓለላቲቨና የተሐድሶ
ሕክምና በማስከተል ዋና ዋና የጤና አገልግሎቶችን
በመሰረታዊ የጤና ተቋማት (primary health care) ማዕከል
ተደራሽ በማድረግ በየደረጃው ደግሞ የሁለተኛ ሦስተኛው
ደረጃ የጤና አገልግሎቶች እንዲቀርቡ ይደረጋል፡፡ በመሆኑም
የዓለም ጤና ድርጅት በተለምዶ ከሚያስቀምጣቸው ስድስቱ
የጤና ሥርዓት አወቃቅሮች (six building blocks of health
system) በተጨማሪ ሁለት አደረጃጀቶችን በመጨመር የጤና
ዘርፉ እንዲዋቀር ይደረጋል፡፡
የጤና አገልግሎት አሰጣጥ
የጤና ባለሙያ የሰው ኃይል
የመድኃኒቶች፣ ክትባት፣ የላቦራቶሪ ፍጆታዎች እና
የሕክምና ቴክኖሎጂ
በጀትና ፋይናንሲንግ
የጤና መረጃ፣ ጥናትና ምርምር፣ ዕቅድ አፈፃጸም፣
ክትትልና ግምገማ
አመራርና አስተዳድር
የዘርፈ ብዙ ምላሽ እና የተጓዳኝ ሁነቶች
የማኅበረሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ፣ ቅስቀሳና
አዲቮኬሲ
161 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !