Page 158 - አብን
P. 158
አብን
እና የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋሙ በሦሥትዮሽ
የሚወስኑበት ስርዓት ይዘረጋል። አብዛኛውን የኃይል
ማስተላለፊያ መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች በመንግስት የተሰሩ
እና ወደፊትም የሚሰሩ ስለሚሆን እነዚህን መስመር ተጠቅሞ
ለሽያጭ የሚያቀርቡ አምራቾች ሃይሉን በቀጥታ ለመንግስት
መሸጥ ይጠበቅባቸዋል።
መ. ልዮ የኃይል ድጋፍ ሥርዓት
የታዳሽ ኃይል የማመንጨት ዘርፍ ውስጥ የሚሳተፉትን
ግለሰቦች ሆነ ድርጅቶች በመንግስት የተለያዩ ማበረታቻዎች
ይደረግላቸዋል። በታዳሽ ኃይል ዘርፍ ለሚሳተፉ በሙሉ
የካርቦን ንግድ ጥቅም፣ የታክስ ቅነሳ፣ ልዮ የብድር
አገልግሎት፣ የመስሪያ ቦታወችን ቅድሚያ መስጠት፣ ለዘርፉ
የተቀላጠፈ አሰራር መፍጠር እና የተለያዮ እገዛወች ማድረግ
ያካትታል።
በግለሰብ ደረጃ የራሳቸውን የኃይል ፍላጎት ከሟሟላት
አልፈው ትርፍ ኃይል ለሚያመርቱ ያመረቱትን ኃይል ወደ
መንግስት ማዕከላዊ ሥርጭት በአደራነት ማስተላለፍ የሚችሉ
ይሆናል። ይህን ኃይል መጠቀም በፈለጉበት በማንኛውም ጊዜ
ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና ክፍያ የማግኝት መብት
አላቸው።
156 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !