Page 156 - አብን
P. 156
አብን
ሀ. ኃይል ማመንጨት
የኃይል ማመንጨት ሂደቱ ከትናንሽ የኃይል አምራች
እስከትላልቅ የኃይል አመንጭ ተቋማት የሚያካትት ይሆናል።
ፖሊሲው በዋነኝነት የአገሪቱን በሁሉም ዘርፍ የመገንባት
አቅም እና እምቅ ተፈጥሯዊ ጸጋ፤ የማምረት ሂደቱ የጎንዮሽ
ጉዳቶች እና ጠቀሜታ ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው። የኃይል
ልማቱ ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ባለኃብቶች ክፍት
ይሆናል። በዚህ ፖሊሲ የኃይል ልማት ዝርጋታ
ያልደረሰባቸው አካባቢወችን በተለየ ትኩረት አነስተኛ ኃይል
ማመንጫወችን በመጠቀም ለወጣቱ የሥራ እድል ፈጠራ
እንዲውሉ ያደርጋል። የመንግስትን የኃይል ተቋም
እንደተቆጣጣሪ በማድረግ የሕዝብ ተቋማትን እና የግል
ባለኃብቶችን ያቀናጀ የኃይል ልማት በልዩ ትኩረት ይሰራል።
የአገሪቱን የማመንጨት አቅም በኃይል ምርምር ተቋሙ
አማካኝነት በተለያዩ ዞኖች በመክፈል እንደአካባቢው የኃይል
ስብጥር እና መጠን በቅደም ተከተል የኃይል ልማቱ
ይፈጸማል።
ለ. ስርጭት እና አጠቃቀም
የኃይል ስርጭቱ በአንድ ማዕከል ማሰባሰብ እና ለተጠቃሚወች
ማሰራጨትን ከሚተገብረው የማዕከላዊነት ሥርዓት በተጨማሪ
ኃይሉ የተመረተበትን አካባቢ በቀጥታ መድረስ የሚያስችል
ሁለተኛ አማራጭ እንዲኖረው ይደረጋል። በዚህም የአገሪቱ
154 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !