Page 160 - አብን
P. 160
አብን
የኃይል ቁጠባ ማስገንዘቢያ ተቋም
ኃይል ከመነጨ በኋላ ከማስተላለፍ ቀጥሎ ኃይል የሚባክነው
በተጠቃሚዎች የአጠቃቀም ጉድለት ነው። ይህን የኃይል
ብክነት ለማስቀረት ከማምረት ጋር በተጓዳኝነት እኩል
መስራት ይገባል። ኃይልን አለማባከን ለአገር ትልቅ ውለታ
እንደመዋል እንዲቆጠር ማድረግ የሚያስችል ከልዮ ልዩ
ባለድርሻ አካላት፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ተቋማትን ያቀናጀ በበጎ
ፈቃደኝነት የሚሰራ ተቋም መመስራት ያስፈልጋል። የኃይል
ቁጠባ ግንዛቤን ለሕዝቡ በቀላሉ ተደራሽ ለማደረግ የሚዲያ
ተቋማትን ይጠቀማል። ይህንን ተቋም በበላይነትም የኃይል
ስርጭት ዘርፉ ይመራዋል።
2.6.3 የተፈጥሮ ጋዝና ማዕድናት
በየአካባቢው መኖራቸው የተረጋገጠና ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ
ማዕድናት የየአካባቢዎችን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ባደረገ መንገድ
ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይደረጋሉ፡፡ ለአገር በቀልና ዓለምአቀፍ
የማዕድን ፈላጊና አልሚ ተቋማትም ልዩ ማበረታቻና ድጋፍ
ይደረጋል፡፡ የአካባቢ ብክለትን በማያስከትል መልኩ የነዳጅና
ተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋና ቁፋሮ ልማት ሥራዎችም ትኩረት
ይሰጥባቸዋል፡፡
158 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !