Page 162 - አብን
P. 162
አብን
ሁሉም ዜጎች የጤና መድኅን ሽፋን ተጠቃሚ እንዲሆኑ
ይደረጋል፡፡ ቁጥርን፣ ጥራት እና ስብጥርን ያማከለና ያገናዘበ
የጤና ባለሙያዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡ የጤና
ተቋማት በሰንሰለታዊ እርከን የሕዝብን አሰፋፈርና
መልካምድራዊ አቀማምጥን ተከትለው ይቋቋማሉ፡፡
እንደአስፈላጊነቱ የረቀቀ ሕክምና የሚጠይቁ ማዕከላት
እንዲገነቡ ይደረጋል፡፡
የባሕል መድኃኒትና ሕክምና የጤና አገልግሎት የሚሰጡ
የእምነት ተቋማትና ቦታዎች ከዘመናዊ ሕክምና ጋር
በተግባቦት ለማኅብረሰቡ የጤና መበልፀግ አዎንታዊ አስተዋፆ
እንዲኖራቸው ይደረጋል፡፡ የባሕል መድኃኒቶቹን በዘመናዊ
ምርምር ለጤና ግብኣትም ሆነ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን
ለሕዝብና ለአገር እንዲያመጡ ልዩ ትኩረት ይደረጋል፡፡
የመድኃኒት አቅርቦት ጥራቱን የጠበቀና ያልተቆራረጠ
እንዲሆን ይደረጋል፡፡ የዜጎች የጤንነት ጉዳይ ከጤናው ዘርፍ
በላይ የሆነን አገራዊ ግብረ-መልስና ትብብር ስለሚጠይቅና
አስፈላጊ በመሆኑ ለጤናው ዘርፍ ግብረ-መልስ የሚሆን
በጠቅላይ ሚኒሰትር ወይም በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የሚመራ
ብሔራዊ ዘርፈ ብዙ ምላሽ መዋቅር እንዲመሰረት ይደረጋል፡፡
ለ. የጤና ሥርዓቱ መዋቅራዊ አደረጃጅት
የጤና ሥርዓት አወቃቅሩ በዋናነት ሁሉንአቀፍ የጤና
ተደራሽነት (universal health coverage) የሚለው
የዓለምአቀፍ መርኅ እውን ለማድረግ በሚያስችል መልኩ
160 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !