Page 157 - አብን
P. 157
አብን
የኃይል ሥርጭት ሁለቱንም የአንድ ማዕከላዊነት እና የቀጥታ
ሥርጭትን በአንድነት የያዘ ይሆናል። ስለሆነም በማዕከላዊነት
ያለውን የኃይል ሥርጭት ጥራት ማሳደግ ላይ ትኩረት
ከሚያደረገው ተደራሽነትን ማስፋፋት በተጨማሪ በግለሰቦች
እና በቡድኖች ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል ሥርጭት እንዲኖር
ይሰራል። በተለይም ከኃይል የመስመር ዝርጋታው ሥርጭት
ማዕቀፍ በርቀት የሚገኝውን ሕዝብ የኃይል ተጠቃሚ
ለማደረግ ታሳቢ ስልት በመንደፍ ይተገበራል። በልዩ ሁኔታ
በቁጥር ትልቁ የአገሪቱ ሕዝብ የሚተዳደርበትን የግብርና ሥራ
ለማዘመን እና የተፈጥሮ ዝናብ ጠባቂነትን ማላቀቅ ትኩረት
ያደረግ የኃይል ማበልጸጊያ ሥርዓት ይዘረጋል።
የአቅርቦት የአጠቃቀም ሥርዓቱ በተለያየ መስፈርቶች
ይወሰናል፤ እነሱም፦
የኃይል ምንጭ አይነት
የአቅርቦት መጠን
የተጠቃሚ ተቋማት አይነት
የማከፋፈል እና የአምራች ተቋማት አቅም
የሥርጭት ሥራዓት እና ሌሎችም መሠረት ያደረገ
ነው።
ሐ. የኃይል ሽያጭ ሕግ
ኃይል አምርቶ ለተጠቃሚ ማቅረብ ለግሉ ዘርፍ ክፍት
የሚሆን ሲሆን ሽያጩን በቀጥታ ለተጠቃሚወችም ሆነ
በመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋሙ በኩል ለሽያጭ ማቅረብ
ይችላሉ። የሽያጭ ዋጋውን አምራቹ፤ የተጠቃሚወች ቦርድ
155 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !