Page 155 - አብን
P. 155

አብን


             ትኩረት  ይሰጣል።  ይህ  ዘርፍ  በመንግስት  ብቻ  የሚሰጥ

             አገልግሎት  ከመሆን  ባለፈ  በግሉ  ዘርፍ  እንደአንድ  አዋጭ
             የኢንቨስትመንት  አማራጭ  መስክ  ተመራጭ  ዘርፍ  እንዲሆን
             እና ብዙ ተቋማት እንዲሳተፉበት ያደርጋል፡፡ ከላይ የተቀመጡ
             ወሳኝ  ዓላማዎችን  ለማሳካት  የሰው  ኃይል  ማሰልጠንና
             የሕብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ላይ ከፍተኛ ትኩረት በማድረግ
             ዓላማውን ያሳካል።

             የአብን  የኃይል  ፓሊሲ  ሌላው  የትኩረት  አቅጣጫ  ፖሊሲው

             ከውጭ  የሚመጡ  የኃይል  ግብዓት  አማራጮችን  በተለይ
             ለትራንስፖርት  አገልግሎት  የሚገባውን  የነዳጅ  ኃይል  በአገር
             ውስጥ  በሚመረቱ  ታዳሽ  ኃይል  በመተካት  እና  ምቹ  የሆኑ
             ቴክኖሎጅዎችን           በመጠቀም         የውጭ        ምንዛሬ      ችግርን
             ይቀርፋል።


             አገሪቱ  አሁን  አብዛኛውን  የኤሌክትሪክ  ኃይል  ከውኃ  ኃይል
             በሚመነጭ  እና  ከውጭ  በምታስገባው  የተፈጥሮ  ነዳጅ  መሉ
             በሙሉ  በሚባል  ደረጃ  ጥገኛ  ስትሆን  ይህ  ፖሊሲ  ሌሎች
             የኃይል  ምንጮችን  ይጠቀማል።  እነዚህም  አማራጭ  የኃይል
             ምንጮች የፀሐይ፣ ንፋስ፣ ኒዩክሌር፣ ከእጽዋት እና ከልዮ ልዩ
             ተረፈ  ምርቶች  የሚመነጭን  ቆሻሻ  በመጠቀም  የሚመረቱ
             ነዳጆችን  ወ.ዘ.ተ  ያጠቃልላል።  የኃይል  አቅርቦት  ስብጥሩንም
             በተወሰኑ  የኃይል  ምንጮች  ላይ  ብቻ  የተንጠለጠለ  ከመሆን

             ይታደገዋል።  ከላይ  የተጠቀሱትን  ዓላማወች  ሁሉ  ተግባራዊ
             በማድረግ  የኃይል  አቅርቦቱን  ወጥነት  ያለውና  ከፍላጎቱ  ጋር
             በተመጣጣኝ እንዲያድግ ማድረግ ይቻላል።


             153    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   150   151   152   153   154   155   156   157   158   159   160