Page 102 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 102
አብን
ነው፡፡ አብን ይህን ለማድረግ ትኩረት ያደርጋል፤ ተገቢ
ማሻሻያዎችንም ያደርጋል፡፡
4. የመንግስት ዕዳ
መንግስተ ያለበት የዕዳ ጫና የሃገሪቱን አጠቃላይ ምርት 58
በመቶ የሚያህል ሲሆን ይህም ከፍተኛ ለሆነ የውጭ ሃገራት
ጣልቃ ገብነትና ሉዓላዊነት ክብር መቀነስ አስተዋፅኦ
አድርጓል፡፡ ሃገሪቱ ያለባትን የእዳ ጫና ለመቀነስ ጠንካራ የሆነ
የወጭ ግንኙነት ፓሊሲን በመቅረፅ በብድር የተገነቡ
ፕሮጅከቶች አፈፃፀማቻን በማሻሻል እንዲከፍሉና ሃገራቱም
ምህረትን እንዲሰጡን አጥብቆ ይሰራል፡፡ ወደፊት የሚገኙ
የሃገርውስጥና የውጭ ብድሮች ለተፈለገ የተለየ አላማ እና
ከዚያም ሚገኘው ጠቀሜታ ብድሩን መመለስ ከማስቻል በላይ
መሆን እንዳለበት ህግና መመሪያዎችን ያወጣል፡፡
2.2.2 አቅርቦትን መሰረት ያደረገ ፓሊሲ
ሀ. ገበያተኮርፓሊሲ
1. ንግድ እና ኢንቨስትመንት ፖሊሲ
የንግድ ሥርዓት
አብን የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ንግድን ማበረታታት
ለኢኮኖሚ ዕድገትም ሆነ ለህዝቦች ማህበራዊ ውህደት እጅግ
በጣም ወሳኝ መሆኑን ይገነዘባል፡፡ ለዚህ ደግሞ የንግድ ፈቃድ
አሠጣጥና ምዝገባን እጅግ የተቀላጠፈ ማድረግ፣ ከላይ
100 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !