Page 104 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 104
አብን
ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡ በአጠቃላይ ንግድ ለብሔራዊ የኢኮኖሚ
ሽግግራችን የሚበረክተው አስተዋጽዖ በቀጥተኛ መንገድ ብቻ
ሳይሆን በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ከማስተሳሰር ጋርም
የሚገናኝ ሆኖ እንዲቀረጽ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በንግዱ ዘርፍ
የተሰማሩ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት ሥርዓታዊ መገለል
ሳይደርስባቸው እኩል መድረክ እንዲፈጠርላቸው ተግተን
እንሠራለን፡፡ የቀጠናውም ሆነ የዓለም አቀፉ ንግድ ኢትዮጵያን
በተሻለ መንገድ ተጠቃሚ የሚያደርግ እንዲሆን ይሠራል፡፡
ልዩ ልዩ ደረጃ ያላቸውን የቀጠናዊ የትብብር መስኮችን
መክፈት ላይ ትኩረት ተደርጎ ይሰራል፡፡ የውጭ ግንኙነታችን
ንግድንና ኢኮኖሚን ሊጠቅም በሚችል ወዳጅነትን በሚሳድግ
መንገድ እንዲከናወን ይደረጋል፡፡
አርሶ አደሮችና ዝቅተኛ አምራቾች ምርቶቻቸው በቀጥታ
ወደተጠቃሚው ወይም ወደውጭ የሚልኩበትን መንገድ
ለመቀየስ በማህበራትና በዩኒየኖች እንዲደራጁ ምቹ ሁኔታዎች
ይፈጠራሉ፡፡ ምርቶችም በተቻለ መጠን እሴት ጨምረው
ወደውጭ እንዲላኩ እነዲሁም ከውጭ ግብዓቶችን አምጥቶ
ኢትዮጵያ ውስጥ ማቀነባበርና መሸጥ የሚያበረታታ ሥርዓት
እንፈጥራለን፡፡
ኢንቨስትመንት
በሚቀጥሉት ዓመታት ወደመዋቅራዊ ሽግግር ሽግግር መግባት
አለብን ስንል በዋናነት በግል ዘርፉ በሚከማቸው ካፒታል
በሚደረግ ኢንቨስትመንት ነው፡፡ ኢንቨስትመንቶች
የሚያስገኙት ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እየተመዘነ ልዩ ልዩ ድጋፍ
102 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !