Page 122 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 122
አብን
መንጋ እና ባሕላዊ አሰራር ወደ ዘመናዊ በማሻሻል
እየተመናመነ የመጣውን የንብ ቀሰም እጽዋት በማልማት እና
የምርት ጥራትን የሚያሻሽሉ ቴክኖሎጅ በመጠቀም ጥራቱን
የጠበቀ ኦርጋኒክ ማር ለገበያ ማቅረብ ትኩረት የሚሰጠው
ነው፡፡
የመሬት አቅርቦት
የእንስሳት እርባታ ከዘርፉ ባህሪ ወሳኝ እና ለምርት ማነቆ
ከሆኑት አንዱ መሬት ነው፡፡ የመሬት እጥረት በእንስሳት
እርባታ ውስጥ በጣም ወሳኝ ችግር ለሆነው የእንስሳት መኖ
እጥረት ምክንያት ነው፡፡አሁን ያለውን ቢሮክራሲ በማሳጠር
በፍጥነት ወደ ተግባር ለሚገባ አርሶ አደር መሬት የማቅረብ
ሥራ አንዱ ሲሆን የመሬት እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች
ምርቱን በኮንትራት አርሶ አደሩ የሚያመርትበትን እና
ባለሀብቶች የማቀነባበር እና ለገበያ በማቅረብ ተሳስረው
የሚሰሩበት ሥርዓት ይመቻቻል፡፡ በሌላ በኩል ከመሬት
ፖሊሲው መሻሻል ጋር ተያይዞ መሬት ከግለሰቦች በመግዛት
እና በመከራየት ችግሩን መቅረፍ ይቻላል፡፡
ምርምር
የምርምር ተቋማትን በማጠናከር የእንስሳት ዝርያን በማሻሻል
እና አዳዲስ ሳይንሳዊ አሰራሮችን በማውጣት የእንስሳት
ምርታማነት እንዲያድግ ይደረጋል፡፡ይህም አዳዲስ ዝርያ
ማላመድን እና በምርምር በማውጣት ለአርሶ አደሩ
ማሰራጨት ቁልፉ ሥራ ይሆናል፡፡
120 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !