Page 127 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 127
አብን
መሠራት ይገባዋል፡፡ ከተሞች ሊመሩ እና ሊተዳደሩ የሚገባው
በቀጥታ በነዋሪዎች በሚመረጡ መሪዎች እንጅ ከላይ ወደ
ታች በሚሾሙ መሪዎች ነው ብሎ አብን አያምንም፡፡
ለ) የመሬት አጠቃቀም
ሰዎች የሚሰሩባቸውና የሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች ጥበቃ
የሚያስፈልጋቸውን የተፈጥሮ ጥብቅ ደን፣የእርሻና የግጦሽ፣
የማዕድንና ሌሎች የመሳሰሉትን አካባቢዎች ባገናዘበ ሁኔታ
መሆን ይገባዋል፡፡ከቅርብ አስርት ዓመታት ወዲህ በተለይ
አብዛኛው የሀገራችን ህዝብ የሚኖርበት ከፍተኛ /Highland/
መሬት ላይ ያለው ህዝብ አሰፋፈር/አከታተም/ ለእርሻ፣ ለግጦሽ
እንዲሁም ደን የነበረውን አካባቢ በማጥፋት ለከተማነት ጥቅም
ላይ አውሏል፡፡አሁን ባለው ሁኔታ የተመሠረቱ ከተሞችን
ዕድገታቸውን ከመሬት ተፈጥሮአዊ አጠቃቀም አኳያ ሳይንሳዊ
ጥናት ላይ የተመረኮዘ የ100 ዓመት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት
እንዲመሩ ማድረግ እንዲሁም አዳዲስ የሚያስፈልጉ የሰዎች
አሰፋፈርና እንቅስቃሴ በተመሳሳይ ለዚሁ የሚሆን ፍኖተ
ካርታ ማዘጋጀት የፖሊሲና ስትራቴጂው አካል ማድረግ
እንደሚገባ አብን ያምናል፡፡
ከተሞቻችን በውስጣቸው ያሉትን የተፈጥሮ ኃብቶችን
ማለትም ወንዞችና ደኖች፣ ታሪካዊ ቦታዎችን፣የሕዝብ
መዝናኛና የስፖርት ቦታዎችን የረሱ ናቸው፡፡ በመሆኑም
ከተሞች ከፖለቲካ አሻጥር ወጥተው አገልግሎት ዘርፋቸው
በባለሙያዎች እንዲመሩ ይደረጋሉ፤ ዘላቂ የከተሞች ፍኖተ
ካርታም ይዘጋጃል፡፡
125 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !