Page 130 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 130

አብን


             ነው፡፡  እነዚህ  አገልግሎቶችና  ተቋማትን  መገንባት  ቅድሚያ

             የሚሰጣቸው የመንግስት ግዴታዎች ይሆናሉ፡፡

             ረ.)የከተማ  ደም  ስር  የሚባሉት  መንገድ፣  የውኃ  አቅርቦትና
             የፍሳሽ  ማስወገጃ፣  የኤሌክትሪክ፣የስልክና  መረጃ  መስመር
             አገልግሎቶች  ናቸው፡፡  አብዛኛው  የከተሞቻችን  ነዋሪ  የእነዚህ
             መሰረተ  ልማቶች  ተጠቃሚ  አይደለም፡፡  አገልግሎቶቹን
             በተሟላ  መልኩ  ለመጠቀም  የቻለውም  ከፍተኛ  የአገልግሎት
             ጥራት  ችግር  ይገጥመዋል፡፡በአጠቃላይ  የከተማ  መሠረተ

             ልማት የሚባሉት ከላይ የተገለጹት አገልግሎቶች አሁን ካለው
             የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትና ከተሞቻችን ካላቸው ፍላጎት አኳያ
             ከተሞቹ ያላቸው አገልግሎት በጣም ኋላ ቀር ነው፡፡ የዲዛይን፣
             የኮንስትራክሽን፣  የክትትልና  የጥገና  እንዲሁም  የማሻሻያ
             ስራዎች  ላይ  ዘመናዊ  የተቀናጀ  የአሰራር  አብዮት  ተግባራዊ
             ይደረጋል፡፡


             ሰ.)የዲዛይንና የኮንስትራክሽን ሥራዎች በሚመለከት
                      የዲዛይን ዝግጅት፡-

                -  የአንድ  ከተማ  ማስተር  ኘላን  ሲዘጋጅም  ሆነ  ሲሻሻል
                    የከተማው  መገለጫ  /Urban  Image/  የሆኑ  እድሜ
                    ያስቆጠሩ  ታሪካዊ  ኅንፃዎችንና  አካባቢዎችን  ያከበረና
                    ያገናዘበ  መሆን  አለበት፡፡በከተሞች  የመንገድ፣  የውኃ፣

                    የኤሌክትሪክ  አቅርቦት፣የፍሳሽ  ማስወገጃ  የስልክና
                    የኢንተርኔት  መስመር  ሥራዎች  የተናበበና  የተቀናጀ
                    የዲዛይን ዝግጅትና ኮንስትራክሽን ሥርዓት ይዘረጋል፡፡


             128    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   125   126   127   128   129   130   131   132   133   134   135