Page 85 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 85

አብን


             ችሎታቸውን  ላስመሰከሩ  ሠራተኞች  ከፍ  ያለ  ጠቀሜታ

             የሚያገኙበትን  ስርዓት  ማስተዋወቅ፣  በዓለም  አቀፍ  ገበያ
             ተወዳዳሪ  ሁነው  እንዲገኙ  የሚመረቱ  ምርቶች  ከፍተኛ
             የጥራት  ደረጀን  ጠብቀው  እንዲመራቱ  ለማድረግ  የሚያስችል
             የሥራ ተነሳሽነት እና የስራ ስነምግባር እንዲኖር ማድረግ ልዩ
             ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡


             የገጠር መንደሮች የሚቋቋሙበትና እየተጠናከሩ የሚሄዱበትን
             የኢኮኖሚ  ስትራቴጂ/መርሃ  ግብር  ተግባራዊ  እናደርጋለን፡፡
             ይህን እውን ለማድረግ የሃገሪቱን የግብርና ዘርፍ እና የገጠር
             አካባቢዎች  እድገት  ተያዥነት  እና  ቀጣይነት  ባለው  ሁኔታ
             በማበረታታት  እና  በማጠናከር  ረገድ  አብን  ልዩ  ትኩረት
             ይሰጣል፡፡  የግብርና  ዘርፍን  ማዘመን  እና  የገጠር  አካባቢዎች
             የሚሻሻሉበትን  ሁኔታ  ማመቻቸት  አብን                    ከፍተኛ  ትኩረት
             የሚሰጠው የፖሊሲ አቅጣጫ ነው፡፡


             ሌላው  አብን  ትኩረት  የሚሰጠው  ጉዳይ  የሃገሪቱን  የምግብ
             መጠባበቂያ  ክምችት  በማሳደግ  የህዝቡ  የምግብ  ደህንነት
             አስተማማኝ  እንዲሆን  ማድረግ  ነው፡፡  ይህን  ለማድረግ
             እንዲቻል፣  ለዘመናዊ  ግብርና  እድገት  የሚያስፈልጉ  የግብርና
             ነክ  ኢንዱስትሪዎች፣  የቢዝነስ  አስራር  ዘዴዎች  በገጠሩ
             እንዲተዋዋቁ እና እንዲጠናከሩ ይደረጋል፡፡


             በገጠሩ  የሀገራችንን  አካባቢ  የሚኖረው  ህዝብ  የኑሮ  ደረጃ
             እንዲሻሻል  ለማድረግ  የገጠር  ዝቅተኛ፣  መካከለኛና  ትልቅ
             ኢንዱስትሪዎች           እንዲቋቋሙ፣          ጀማሪ       የምርት        እና
             የአገልግሎት  ተቋሞች  በእግራቸው  እንዲቆሙ  የሚያስችል
             የፋይናስ  ድጋፍ  እንዲቀርብ፣  የገጠሩ  ኢኮኖሚ  የሚደገፍበትና

               83   ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   80   81   82   83   84   85   86   87   88   89   90